Thursday, September 19, 2013

ብሶት የወለደው ጀግናው የግንቦት 7 ህዝባዊ ታጣቂ ሀይል

አምባገነኑ የወያኔ መንግስት የኢትዮጲያን ህዝቦች በግዴታና ፍትህ በተጕዋደለ ግዞት ረግጦ ሲገዛ  22ኛ አመቱን አስቆጥሮ አሁንም የሰባዊ መብት ረገጣን እለት ከእለት እያባባሰ አገራችን ኢትዮጵያ እንዳገር የመቀጠሉዋን ዋስትና ከጥርጣሬም ባሻገር ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከቷታል ፣ አገዛዙ የፈጠራቸው የእርስ በርስ የዘር ክፍፍል እና ጥላቻ ፣ የሰባዊ መብት አፈና እና የእስር ቤቶች በንጿሃን ዜጎች ለእውነት በቆሙ እና ላገር ለወገን ተቆርቋሪ ግለሰብ ጋዜጠኞች እንዲሁም የተቃዋሚ ድርጂት አባላት እና መሪዎች ማጎሪያ መሆን፣ በገዛ አገራቸው በልማት ሰበብ እና ስም ዜጎችን ከቀያቸው  ያለአግባብ በማፍናቀል ህገ ወጥ ድርጊት እየፈጸመ እንዳሻው ከህግ እና ደምብ በላይ መሆኑን  ቀጥሎል።

ስለሆነም ለአመታቶች በገዠው መንግስት ሲጭቆን እና ሲረገጥ የኖረው ህዝብ በቃኝ ብሎ ተነስቱዋል። ህዝቡ ብሶቱን በተለያየ የሰላማዌ ህዝባዊ አምጽ ከማሰማቱም ባሻገር በዚሁም ምክንያት በሚደርስበት እስር እና እንግልት እንዲሁም የማስፈራራት ዛቻ ሳየበገር አሁንም የግፍ አገዛዙ በቃን መረረን የወያኔ እንደገዠነት የመቀጠል ህልውና ሊያበቃለት ግድ ይላል ብሎ ቆርጦ ተነስቱዋል ።
ህዝባዊ የሰላም አመጻን በዷላ እና በእስተኛር ስቃይ ሊያቆም ያልቻለው ወያኔ አሁን ደሞ ከጎኑ ብሶት የወለዳቸው የኢትዮጲያ የቊርጥ ቀን ልጆች ግንቦት 7 ህዝባዊ ታጣቂ ሀይል ተነስቶበታል ። ትጥቄን የሚያስፈታኝ የታጠቀ ብቻ ነው አለያ ስልጣኔን በሰላም እና በምርጫ  አለቅም ያለው  እምቢተኛው ገዢ ሌላ ጉድ እና ውርደት እንዲሁም የስልጣን ኪሳራ ሊደርስበት ነው።

ይህንኑ አዲስ የሆነውን የግንቦት 7 ህዝባዊ ታጣቂ ሀይል፡ የተማሩ ሀይሎች ፡ ድፍረትና ቁርጠኝነትን የተላበሱ ወጣቶች የተሰባሰቡበት ሲሆን፡ እንዲሁ ከአገር ቤት እና ከተያዩ የውጭ አገራት፡  በገዢው አገዛዝ ግፍ ተማረው ሸሽተው የተሰደዱ ኢትዮጲያዊያኖች እየተቀላቀሉዋቸው ይገኛሉ።

እንዲሁም በቅርቡ በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት አብራሪዎች ፣ የበረራ አስተማሪዎች ስርአቱን ከድተው ግንቦት7ትን መቀላቀላቸው ታውቋል።
ከኢትዮጵያ አየር ሀይል በመለየት ግንቦት 7ትን መቀላቀላቸውን ለኢሳት ያረጋገጡት የበረራ ባለሙያዎች በአየር ሀይል ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አድሮ ለርምጃው እንደገፋፋቸው አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከዘረኝነትና አድሎው ባሻገር በሰራዊቱ ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ተቋሙን ለቀው የነጻነት ታጋዮችን ለመቀላቀል እንዳስወሰናቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በአብራሪትና በበረራ አስተማሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው ስርአቱን የተለዩት አራቱ የበረራ ባለሙያዎች ካፒቴን አክሊሉ መዘነ፣ ካፒቴን ጥላሁን ቱፋ፣ ካፒቴን ጌቱ ወርቁና ካፒቴን ቢንአም ግዛው ናቸው።

በ1998 ኣም በሶማሊያ ከእስላማዊ ህብረት ሀይሎች ጋር በተደረገው ውጊያ ተሰታፊ እንዲሁም በዳርፉር የሰራዊት ማስከበር ተልእኮ የዘመቱት እነዚህ የበረራ ባለሙያዎች ሁለቱ ለከፍተኛ ትምህርት ከተላኩት ቻይና ተመልሰው ትግሉን መቀላቀላቸውን ሲገልጹ ሁለቱ ደግሞ ከሳምንት በፊት ድሬዳዋ ከሚገኘው የአየር ሀይል ምድብ ተነስተው ስርአቱን መክዳታቸው ተመልክቷል። በቅርቡ የመረጃ መኮንን የነበረው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ግንቦት7ትን ተቀላቅሏል።
በአሁኑ ጊዜ በርካታ ወጣቶች ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ መሆኑን ብዙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በተጨማሪም በመላው አለም የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጲያውያኖች እና ትግሉን የሚደግፉ ግለሰቦች በሚችሉት ሁሉ የገንዘብ እርዳታ ድጋፋቸውን እየለገሱ ሲሆን በቅርቡ መስከረም 28፣2013 በኖርዌይ ኦስሎ የሚደረገው ታላቅ የግንቦት 7 ህዝባዊ ታጣቂ ሀይል  የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ከወዲሁ ስኬታማ እየሆነ ነው።

ስለሆነም አገር ወዳድ የሆናችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ የበኩላችሁን አስተዋጾ ለቁርጠኛው ግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይል ድጋፍችሁን አበርክቱ እላለሁ

Ethiopian journalist on hunger strike over mistreatment in prison

IMWF calls for reinstatement of visitation privileges
September 13, 2013 -- As stories about the political crisis in Cairo have been dominating the news from Egypt, there has been limited coverage on a brewing international conflict between Egypt and Ethiopia – two countries that do not share a border but are indivisibly connected by the Nile, the world's longest river.
Amid works to construct a giant hydro-electric dam, and much to the anger of the Egyptian government, Ethiopia has started diverting the Blue Nile, a tributary of the Nile, prompting a furious debate about if and how the “Great Ethiopian Renaissance Dam” will affect Egypt's water security.
While there may not be a definite answer anytime soon on whether this dam will have any impact on water security in Egypt, there is no doubt that it has already negatively impacted press freedom in Ethiopia. Earlier this summer, for instance, the Committee to Protect Journalists reported that Ethiopian officials arrested a reporter seeking to interview people evicted from their homes in the region where the contentious hydro-electric dam is being built. More notable, however, was the arrest of Ethiopian columnist Reeyot Alemu more than two years ago.
A critic of the government writing for the now-defunct newspaper Feteh, Alemu had raised questions about the funding and merits of the dam shortly before she was arrested on bogus terrorism charges and sentenced to 14 years in jail.
Although two of the three terrorism charges against her were later dropped on appeal and her sentence reduced to five years, Alemu continues to suffer from her government's efforts to silence dissenting voices and scare independent journalists into self-censorship. A tumor in Alemu's breast remains untreated as she is denied access to medical care, and threats of solitary confinement linger over her every move in Ethiopia's notoriously ill-maintained Kaliti prison.
While the Ethiopian leadership insists on the country's adherence to the rule of law, there seems to be little doubt in the international community that Alemu's arrest and conviction was politically motivated: The International Women's Media Foundation honored Alemu with its Courage in Journalism Award last year, and in May 2013, the United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO) recognized her “commitment to freedom of expression” with itsGuillermo Cano World Press Freedom Prize. In July, a delegation of the European Parliament's Subcommittee on Human Rights, scheduled to meet with Alemu, was denied access to Kaliti prison, prompting questions by members of the European Parliament over Ethiopia's commitment to human rights.
According to the Committee to Protect Journalists, Ethiopia jailed more journalists than any other country in Africa in 2012 (with the exception of Eritrea), and 45 Ethiopian journalists have been forced into exile since 2008. Swedish journalist Martin Schibbye who gained first-hand experience with Ethiopia's crackdown on press freedom after being arrested there himself in June 2011, delivers a damning verdict on the rule of law in Ethiopia: "There is no such thing as an independent justice system, it's completely politicized. If the order comes from the federal level that Reeyot is to let go, she will be free. But if they feel that they gain more from keeping her in prison, they will keep her locked up. This decision lies entirely in the hands of the Ethiopian government," he said.
But the Ethiopian authorities seem to be determined to keep Alemu silenced. Earlier this week, as Ethiopians were preparing for their New Year's celebration, prison officials denied Alemu visits from anyone but her parents. It remains unclear whether the decision to keep her separated from her friends, siblings, and fiance is in response to an open letter Alemu wrote in August, criticizing Ethiopia's Anti-Terrorism Proclamation, but it appears to be unlikely that the timing of the new restrictions is coincidence.
Protesting the prison's decision to deny her visits from friends and relatives, Alemu has gone on hunger strike. The IWMF is deeply concerned about Alemu's health and well-being, and calls on the decision-makers at Kaliti prison to re-instate Alemu's full visitation privileges immediately.

Sunday, June 30, 2013

« ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ጄ/ል ሳሞራ

 የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት የነአዜብ/በረከትን ቡድን በመቃወም ከነስብሃት ቡድን ጋር በመሰለፋቸው እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል። የጠ/ሚ/ር መለስን ሕልፈት ተከትሎ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ስር እየሰደደ መሄዱንና የልዩነቱ መንስኤም በሕወሐት የተፈጠረው ቀውስ – ጄነራሎቹ ጎራ እንዲለዩ ጫና ማሳደሩን ያመለከቱት ምንጮች፣ አክለውም ልዩነቱ በአገር ጉዳይ ዙሪያ ሳይሆን አንዱ ሌላኛውን በማስወገድ የራስን ጥቅም አስጠብቆ በስልጣን ለመቆየት የሚደረግ የሙስና መጠላለፍ ነው ብለዋል።
ጄ/ል ክንፈ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት በሟቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ እንደሆነ ያስታወሱት ምንጮቹ ከስልጣን ሊያግዳቸውም ሆነ ሊያወርዳቸው የሚችለው በህግ ስልጣን የተሰጠው ጠ/ሚኒስትሩ መሆኑን ያስረዳሉ። በዚሁ መሰረት ስልጣኑ በአዋጅ የተቀመጠው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪይም ቢሆንም – በግልፅ የሚታየው ግን ከህግ ውጭ የጄ/ል ሳሞራ ፈላጭ ቆራጭ ውሳኔ ከመሆኑ በተጨማሪ የታገደውን ጄ/ል ወደ ቦታው የሚመልሰው በተቃራኒው የቆመውና በሕወሐት ውስጥ ያለው የነስብሃት ቡድን መሆኑን ምንጮቹ ያመለክታሉ። አቶ መለስ ይዘውት የቆዩትና “በሕገ-መንግስቱ ተሰጠ” ከተባለው ስልጣን በአብዛኛው ለጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም ሊሰጥና ሊተላለፍ አልቻለም ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ ቁልፍ የሆነው የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነትን ጨምሮ በርካታዎቹ ሕገ-ወጥ በሆነ ሁኔታ በሕወሐት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቃቸውን አመልክተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ- ጄ/ል ሳሞራ የሚመሩት ስብሰባ በመከላከያ ከፍተኛ ጄነራሎች ተሳታፊነት በዚህ ሳምንት ሲካሄድ መሰንበቱን ምንጮች ጠቆሙ። ውጥረትና ያለመረጋጋት በተስተዋለበት የሳሞራ ንግግር በዋና አጀንዳነት የቀረበው የግንቦት ሰባት ጉዳይ ሲሆን በዚህም ፥ « ግንቦት ሰባት በመንግስትና በሕገ-መንግስቱ ዙሪያ መጠነሰፊ አደጋ ጋርጦብናል፤ በግንቦት ሰባት የሚደገፉ በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ልንወስድ ይገባል፤» ማለታቸውን የገለፁት ምንጮቹ፣ ሳሞራ «ለምሳሌ.» ሲሉ ሰማያዊ ፓርቲን እንዲሁም « አንዳንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች» በማለት መፈረጃቸውን አስታውቀዋል። በተጨማሪ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እያነሳ ያለውን ፍትሃዊ የመብት ጥያቄ፣ ሳሞራ ከግንቦት ሰባት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በሌላም በኩል የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ሃላፊ ብ/ጄነራል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ በበኩላቸው፥ ከእንግሊዝ አገር ረቀቅ ያለ መሳሪያ በማስመጣት በስካይፕ ተቃዋሚዎች የሚያደርጉትን ግንኙነቶች በመጥለፍና ተዛማች የስለላ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ከገለፁ በኋላ « ግንቦት ሰባት ከግብፅ ጋር ግንኙነት እንዳለው ለህዝቡ ከነገርነው ከጎናችን ይቆማል፣ ግንቦት ሰባትን በማውገዝ የእንቅስቃሴው ተባባሪ አይሆንም፣ በአገር ውስጥ ያሉትም ተቃዋሚዎች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ህዝቡ አይቃወምም፤ እንዳውም ለመንግስት ድጋፍ ይሰጣል፤» በማለት በተሰብሳቢ መኮንኖች ጭምር ገረሜታን የፈጠረ ንግግር ማድረጋቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል። በዚህም ለሕዝብ ያላቸውን ግምትና የግንዛቤ ደረጃ ያመላከተ ነው ያሉት ምንጮቹ የጄ/ል ተክለብርሃን የእውቀት ደረጃ ምን ድረስ እንደሆነ ያሳየ ነው ብለዋል። የኤንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በአቶ ደብረፂዮን ጭምር በበላይነት እንደሚመራና አቶ ሃ/ማሪያም የሚያውቁት እንደሌለ ምንጮቹ አያይዘው ጠቁመዋል። በሕገ – መንግስቱ መከላከያ ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ እንደሆነ ቢደነግግም፣ ከወረቀት በዘለለ ተግባር ላይ ሲውል እንደማይታይና የነሳሞራና ተከታዮቻቸው ተደጋጋሚ አቋምና ተግባር በቂ ማስረጃና ማሳያ መሆኑን ምንጮቹ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል።
በመጨረሻም፥ የታገዱ ሌሎች ጄኔራሎችን ጉዳይ እንዲሁም ባለፈው ወር በሳሞራ ትእዛዝ የተባረሩ የሕወሐት ጄነራሎች ወደ ከፍተኛ ንግድ መሰማራት በተመለከተ ዝርዝር መረጃውን ይዘን እንመለሳለን።(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

Tuesday, June 25, 2013

“ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር አሰሩኝ ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር ዝዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መታሰርህን ለቤተሰብ ተናግረሀል?
ወጣት ተስፋዬ:- ለማንም ሰው እንድናገር አልፈቀዱልኝም፤ መስሪያ ቤቴ አልጠየቀኝም፣ ደሃዋ እናቴ ያለችው ናዝሬት ነው እሷም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አባቴ አቶ ተካልኝ አስተማሪ ነበር አርባ ጉጉ ላይ ነው በ1985 ዓ.ም በነበረው ግጭት ነው የተገደለው፡፡ ማንም ሳይጠይቀኝ፣ፍ/ቤት ሳልቀርብ 23 ወር ታሰርኩ ልብስ ምግብም የሚያመጣልኝ ሰው አልነበረም፡፡ እናቴም መታሰሬን እንኳ አታውቅም መስሪያ ቤቴም ስኮላርሽፕ አግኝቷል፤ ወደ ውጪ ሃገር ሊማር ሊሄድ ነው የሚባል ነገር ስለነበረ አልጠየቁኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የት ነበር ስኮላርሺፕ ያገኘኸው?
ወጣት ተስፋዬ:- የዛሬ 2 ዓመት አካባቢ የራስመስ ሙንደስን ስኮላርሽፕ አግኝቼ ነበር፡፡ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያና ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶክዮ ባሉ ምሁራን ሪኮመንድ ተደርጌ በጣሊያኑ ፌራሪ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ እንደተፈታሁ ሄጄ ስጠይቃቸው ብዙዎቹ ጓደኞቼ በጣም ደነገጡ፡፡ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ቅማል ተወርሬ … ባካችሁ ተውኝ … ምንም የሌለ ነገር የለም በጣም ተጎድቻለሁ፡፡ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ እናቴ ጋ ስሄድ በጣም ደነገጠች፣ በሕይወት ያለሁ አልመሰላትም 23 ወር ሙሉ ከቤተሰብ ስለተለየሁ ግራተጋባች፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- በእስር ወቅት የደረሰብህ ድብደባና ማሰቃየት ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ በኤሌክትሪክ ጀርባዬ ላይ አቃጥለውኛል፣ በብልቴ ላይና በኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱብኝ ሽንት ችዬ አልሸናም፣ ሽንቴን መቆጣጠርም አልችልም፡፡ ኩላሊቴንም በጣም ያመኛል፡፡ ውሃ ውስጥ እየነከሩ በጣም ደብድበውኛል፡፡ አሁን ስናገር ያመኛል ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደው ስታስበው ለእስር ያበቃህ ወይም ከመንግስት ጋር ያጋጨህ አጋጣሚ ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- መስሪያ ቤቴ ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፤ በጣም ይከታተሉኛል፡፡ በቢ.ፒ.አር ላይ ስብሰባ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ እኔም ሠራተኛ ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ነገሮች ሲመጡ እኔ አልቀበልም በግልፅ እናገር ነበር፤ ሠራተኛውም እኔን ይደግፋል፡፡ ከመታሰሬ ጥቂት ጊዜ በፊት ገነት ሆቴል ስብሰባ ነበረን፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ በጣም ተከራከርኩ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አቶ ፀጋዬ ማሞ የሚባሉ አሰልጣኝ፣ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከንግድና ኢንዱስትሪም የመጡ ነበሩ ስማቸውን የማላስታውሳቸው ባለስልጣን ነበሩ፤ እዛ ላይ ሀሳብ አንስቼ ተከራክሬ ነበር፡፡ “የሠራተኛን ሀሳብ ዳይቨርት ያደርጋል” ይሉኝ ነበር፡፡ መቼም ግን ሀሳቤን በመናገሬ ይህን የመሰለ ስቃይ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ “አሸባሪ፣ ግንቦት ሰባት” እያሉ እኔ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ያለምንም ፍርድ በርሜል ውስጥ ውሃ ጨምረው እያስተኙ አሰቃዩኝ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደዚህ ያሰቃዩህ ምን አይነት ምንም አይነት መረጃ ሳያገኙ ነው?
ወጣት ተስፋዬ:- እኔን ጥፋተኛ የሚያስደርግ ምንም መረጃ አላገኙም፣ እኔን አስረው ወደ መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ይደውሉ እንደነበር ይነግሩኝ ነበር፡፡ የኢሜይል አድሬሴንም ተቀብለው በርብረዋል ግን ምንም አላገኙም፡፡ እኔ ከማንም ጋር ሊንክ የለኝም ኢሜሌ ላይ የስኮላርሺፕ መልዕክት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለውም፡፡ በመስሪያ ቤቴ ሪሰርቸር ነበርኩ፣ በሶሲዮሎጂ ነው የተመረኩት፡፡ ሉሲ የተገኘችበት ሣይት ላይ አፋር፣ ጋምቤላ ብዙ ሳይቶች ሰርቻለሁ፡፡ ከአለቆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሰላማዊ ነው እነሱ ናቸው ስኮላርሽፕ ሪኮመንድ ያደረጉኝ፡፡ አንደኛው ፕሮፌሰር 25 ዓመት ሙሉ እዚህ አገር ሰርቷል፣ አርዲን ያገኘው እሱ ነው፡፡ ሄነሪ ጊልበርት ይባላል፤ እሱም ሪኮመንድ አድርጎኛል፡፡ እኔ በጣም የሚቆጨኝ ደሃዋ እናቴ አረቄና ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ ምን ብዬ ልንገራት እንደዚህ አትጠብቀኝም ከበደኝ፣ አሁን እሷ የምትሰጠኝ ምግብ ራሱ ደምደም አለኝ… (ረጅም ለቅሶ)፡፡ ልጄ በደህናው አይደለም የጠፋው ሞቷል ወይም መኪና ገጭቶታል ብላ ነበር የምታስበው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የከመታሰርህ በፊት ፖለቲካ ተሳትፎ ነበረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- 1997 ዓ.ም የቅንጅት ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ በ97 የነበረው ሁኔታ ስንት ሰው አለቀ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር ታውቃላችሁ ምንም የምናደርገው ነገር አልነበረም ፡፡ በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል ተረዳሁኝ፡፡ ከ1997 ዓ.ም በኋላ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልሆንኩም፡፡ ከዚህ በኋላ ከምንም ነገር የተገለልኩ ሆኛለሁ፡፡ አንድ ብርጭቆ ሳትሰብር አሸባሪ ስትባል አስብ እንግዲህ አንድ ብርጭቆ እንኳን ሰብሬ አላውቅም ባለኝ እውቀት እንደውም ለእውቀት ነው የምጓጓው እውቀቴን አሳድጌ አገሬን ለመለወጥ ነው የማስበው እኔን ምንም የሚመለከተኝ ነገር የለም አሸባሪም ግንቦት ሰባትም አይደለሁም፡፡ስትደበደብ፣ ስትሰቃይ ያላደረከውን አድርጌያለሁ ትላለህ፤ በርሜል ውሃ ሞልተው ይከቱሃል ያሰቃዩሃል፡፡ አያሳዝንም ይሄ? እንዴት አድርጎ እዚህ አገር ይኖራል? 23 ወር ሙሉ አስረው ማሰቃየታቸው ሳያንስ የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም ብዬ ነው የነገርኳችሁ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን የት ነው የምትኖረው?
ወጣት ተስፋዬ:- መኖሪያ የለኝም … (ረጅም ለቅሶ)
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝን ለመርዳት የምትፈልጉ አንባብያን ከፍኖተ ነፃነት መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ (ምንጭ ፍኖተ ነጻነት)

Sunday, June 16, 2013

በሌሊት እርቃኔን ሆኜ ቀዝቅዛ ውሃ እየተደፋብኝ ምርመራ ይካሄድብኛል

በሌሊት እርቃኔን ሆኜ ቀዝቅዛ ውሃ እየተደፋብኝ ምርመራ ይካሄድብኛል” - ወ/ሮ አልማዝ
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለፈው ወር ወደ ፍ/ቤት ባቀረባቸው ተጠርጣሪዎች ላይ የጀመረውን ምርመራ እንዳላጠናቀቀ በመግለፁ፤ ለሦስተኛ ጊዜ የ14 ቀናት ቀጠሮ ተፈቅዶለት ተጠርጣሪዎች በእስር እንዲቆዩ ታዘዘ፡፡ በአምስት የምርመራ መዝገቦች የተካተቱት ከአርባ በላይ ተጠርጣሪዎች ሰሞኑን እንደገና ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ከተጠርጣሪዎች አንዷ የሆኑት ወ/ሮ አልማዝ ከበደ በውድቅት ሌሊት ራቁታቸውን ቀዝቃዛ ውሃ የተደፋባቸው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ለፍ/ቤቱ ገልፀዋል፡፡ ፍ/ቤቱ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በተለያዩ መዝገቦች የቀረቡት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ነጋዴዎች፣ ትራንዚተሮችና ደላላዎች እንዲሁም የገቢዎችና ጉምሩክ ሠራተኞች የጠየቁትን የዋስትና መብት በመከልከል የምርመራ ቡዱኑና አቃቤ ህግ ለ3ኛ ጊዜ የጠየቁትን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ካሁን በፊት ተጠርጣሪዎቹን የያዝኳቸው በበቂ ማስረጃ ነው ማለቱን ጠቅሰው፣ ምርመራዬን አልጨረስኩም እያለ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ አልነበረበትም ብለዋል፡፡
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሁለቴ የ14 ቀን የቀጠሮ እንደተሰጠው የተጠርጣሪ ጠበቆች ገልፀው፤ ኮሚሽኑ ምርመራዬን አላጠናቀቅኩም ብሎ እንደገና ጊዜ ይሰጠኝ ማለቱ ስራውን በትጋት እየተወጣ አለመሆኑን ያመለክታል ብለዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን በበኩሉ፣ እስካሁን ያከናወናቸውን ስራዎች ለፍርድ ቤቱ ሲዘረዝር በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤትና ቢሮ በብርበራ የተገኙ ሠነዶችን ሲያጣራ መቆየቱን ጠቅሶ፣ ዲጂታል ማስረጃዎችን ለሙያተኛ በመላክ ውጤቱን እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ በሞጆ፣ በአዳማ፣ በሚሌ እና በአዋሽ የገቢዎችና የጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የምርመራ ቡድን ተልኮ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ለፍ/ቤት ተናግሯል፡፡ ቀረጥ ሰውረዋል ተብለው በተጠረጠሩት ድርጅቶች ላይ የተጀመረው የኦዲት ስራ አለመጠናቀቁን የገለፀው ኮሚሽኑ፤ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ የኦዲተሮችን ቃል እቀበላለሁ ብሏል፡፡
ምንጩ ያልታወቀ ሃብትን ህጋዊ አስመስሎ ከመያዝ ጋር በተገናኘ የተጀመሩ ምርመራዎችም እንዳልተጠናቀቁ ኮሚሽኑ ገልፆ፤ ፍ/ቤቱ የምርመራውን ስፋት እና ውስብስብነት በማገናዘብ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይፍቀድልኝ ሲል ጠይቋል፡፡ ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን አይቶ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡ ካሁን በፊት በርካታ ተጠርጣሪዎች የተለያዩ በደሎች እና ድብደባ ጭምር እየተፈፀመባቸው መሆኑን በመግለፃቸው ጉዳያቸው እንዲመረመር በፍርድ ቤት የተሰጡ ትዕዛዞች የት እንደደረሱ ባይታወቅም፣ በዚህ ሳምንትም ከተጠርጣሪ ለቀረበ ተመሳሳይ አቤቱታ ተመሳሳይ የምርመራ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ከተጠርጣሪዎች አንዱ የሆኑት ወሮ አልማዝ ከበደ፣ በምርመራ ወቅት ሰብአዊ ክብራቸውን የሚነካ ነገር እየተፈፀመባቸው መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ገልፀው፣ ከምሽቱ 6 ሰዓት ራቁታቸውን ቀዝቃዛ ውሃ እየተደፋባቸው ምርመራ እንደሚካሄድባቸው ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ አልማዝ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ ሲያቀርቡ ቤተሰቦቻቸው ያለቀሱ ሲሆን፤ የፀረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን ድርጊቱን ተቃውሟል፡፡ ተጠርጣሪዎች ያቀረቡት አቤቱታ “ሃሰት ነው” ሲል ተቃውሞ ያሰማው የፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የተጠርጣሪዋ አቤቱታ የተቋሙን ስም ለማጉደፍ ታስቦ ቤተሰቦቻቸው ጭምር የተሣተፉበት በምክክር የተደረገ ነው ብሏል፡፡ በሌላ ትዕዛዝም የህክምና እና ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር ተያይዘው ከተጠርጣሪዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን በተመለከተ የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን እንዲያጣራና ክትትል እንዲያደርግ ፍርድ ቤቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

Friday, June 7, 2013

Remembering the June 2005 Massacres

On 8th June 2005, TPLF’s heavily armed Agazi forces, which were directly controlled by Meles Zenawi, were deployed in the streets of Addis Ababa.
They massacred innocent civilians for taking part in a demonstration demanding the respect of the outcome of the elections in the country.
Most of the dead had gunshots to the head and hundreds were wounded while thousands were abducted and sent to remote military prison camps.
These murders are regularly referred to just in numerical statistics. But each of this numbers represent fellow Ethiopians, with dreams, loved ones and life plans.
Below are a few descriptions on what happened in the two days of the start of the still ongoing massacres,
8th June 2005: EPRDF’s heavily armed forces deployed in the streets of Addis Ababa massacre at least 42 innocent civilians for taking part in a demonstration demanding the respect of the outcome of the elections in the country. Most of the dead had gunshots to the head and hundreds were wounded while thousands were abducted and sent to remote military prison camps.
8th June 2005: Business owners, taxi and mini-bus drivers take strike action to protest over the ruling party’s alleged massive election fraud and its fierce violations of human rights. The streets of Addis Ababa under the intimidating control of the TPLF’s armed forces. The government places opposition leaders under house arrest.
9th June 2005: Amnesty International issues a press release saying that ‘over 1,500 students and other demonstrators are at risk of torture [and] further arrests are reportedly continuing in Addis Ababa and in other towns where student demonstrations took place’. The organization condemns the excessive use of force by the police, who it says ‘used live ammunition against peaceful protestors’. ‘The excessive and indiscriminate use of force is in contravention of international human rights standards,’ said Kolawole Olaniyan, Amnesty International’s Africa Programme Director.
Below are a few pictures of our Ethiopian Brothers and Sisters of the 2005 post election victims of TPLF’s massacres;
Shibire Desalegn
is believed to be the first victim of the regime’s atrocious killings following the election crisis.

Tuesday, June 4, 2013

ተጠርጣሪዎች ከተከሳሽነት ወደ ምስክርነት

የፌደራል የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ ሳያሰባስብ ክስ መስርቶ ይረታል በሚል የሚታማ ተቋም ነው። ኮሚሽኑ ከጊዜ ወደጊዜ አቅሙንና ልምዱን በማዳበር ከዚህ ችግር መውጣቱን በዳታ አስደግፎ በመግለጽ ይከራከራል። አንድም ሰው ቢሆን ለምን ያለ በቂ ማስረጃ ይታሰራል ለሚለው የሰብአዊነትና የመብት ጥያቄ ያለመረጃ አስሮ ሲረታ ካሳ ስለመክፈሉና ላጠፋው ጥፋት የሚመጥን ቅታት ስለመቀጣቱ ተሰምቶ አያውቅም። የዘወትር ቅዳሜው ጋዜጣ አዲስ አድማስ በዚህ መልኩ ይሁን በሌላ አንድ አስገራሚ ዜና ይዞ ብቅ ብሏል።

ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት ጋር በተያያዘ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ ካካሄደባቸው 125 ተጠርጣሪዎች መካከል በ58 ላይ ክስ ሲመሰርት 52ቱ ከክስ ነፃ ሆነው በምስክርነት እንዲቀርቡ ሊደረግ መሆኑን ምንጮች ገልጾ አዲስ አድማስ አስታውቋል። በምስክርነት ለመቅረብ ተስማምተው ከክስ ነፃ ከሆኑት ምስክሮች መካከል አምስቱ ባለሃብቶች መሆናቸውና ሌሎቹ ደግሞ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን እንዲሁም በተጠርጣሪ ባለሃብቶች ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ መሆናቸውን አዲስ አድማስ አስታውቋል። ጋዜጣው ቀንጭቦ ያሰራጨው ዜና ሰዎቹ አስቀድሞ የታሰሩበትን ምክንያት አመልክቷል።

ከክስ ነፃ የሆኑት ምስክሮች ከሙስና ተጠርጣሪዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ቢሆንም ተሳትፎአቸው በጅምር የቀረና ያልተፈፀመ መሆኑን የጠቆሙ ምንጮች፤ ለፀረሙስና ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት ለምርመራ ስራው አስተዋፅኦ ያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ምስክሮቹን በቅርበት ስለሚያቋቸው ጉዳት ሊያደርሱባቸው ይችላሉ በሚል ማንነታቸው በሚስጥር እንደሚያዝ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምስክርነት ከመስጠትም በተጨማሪ ገና ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችንና ማስረጃዎችን በእነዚህ ምስክሮች አማካኝነት ለማግኘት እየተሞከረ ነው ተብሏል፡፡

Wednesday, May 29, 2013

Refusing a ‘diminished self’

Informed by prison experience, activist-scholar imagines a more open Ethiopia

Most apt of all her local connections, perhaps, is her role as a HarvardScholar at Risk. The program — based in New York, with dozens of affiliates at universities across the world — guarantees a year or more of refuge for scholars, writers, and scientists who in their native lands are under threat of death, imprisonment, or harassment.
“I was in prison because I spoke,” said Midekssa.
She was first sent to prison in 2005 — entering when her daughter Halley was 8 months old — and then again in 2008. Both times she was sentenced to life (the second time her original sentence was death). Both times Midekssa was pardoned because of pressure from international human rights groups. But she was ready to live her whole life in a cell. “I was being imprisoned for a right cause. What else could I do?” said Midekssa. “If you restrain your self-expression, you are left with what? Your diminished self.”
Midekssa had entered Ethiopia’s political arena in 2002 after serving nearly six years on that nation’s federal criminal bench. “Most of my years were full of challenge,” she said of being a judge — a struggle to “keep my independence and professional standards.” While she was on the bench, Ethiopian officials routinely tried to influence her decisions, she said. But she refused to go along, despite pressure that sometimes ratcheted up to threats of death. Her most notorious act of defiant honesty was to free a former defense minister, Siye Abraha, who’d been accused of corruption on dubious grounds, charges that had already cost him years in prison. (Abraha himself was in the Mason Program at Harvard Kennedy School, from 2011 to 2012.)
From girlhood, Midekssa had been enthralled by the idea that Ethiopia one day could be an open democracy, despite the fact that such a concept remained entirely theoretical during her early life. She was born in 1974, the last year of a dynasty of Ethiopian emperors that had started in the 13th century, and grew up in the capital city of Addis Ababa during a military dictatorship that lasted 17 years, ending when she was a senior in high school.

Friday, May 24, 2013

እኛንም ሆነ መጪውን ትውልድ ዋጋ እንዳያስከፍሉን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ እናምናለን።

ሰሞኑን ኢህአዴግ ጉባኤውን ሲጨርስ “አድርባይነት አሰጋኝ” ብሎናል። አባላቶቼ አድርባይ ሆነዋልና በዚህ ከቀጠልኩ እሰምጣለሁ የሚል ስጋት እንዳለበትም አስታውቆናል። ከፍርሃቻው ብዛት የተነሳ አድርባይነትን ለመዋጋትና “መድረክ ላይ ለመጥለፍ” በቁርጠኛነት እንታገላለን ብለው አቋማቸውን ነግረውናል። የሚገርመው ግን አድርባይነትን የፈጠረና ያነገሰው ራሱ ኢህአዴግ መሆኑን መዘንጋቱ ነው።
ኢህአዴግ አድርባይ ሚዲያዎች አሉት። አድርባይ ባለሃብቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ የኔቢጤዎች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይና የማደናገሪያ ፕሮጀክቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ ድርጅቶች እንጂ ነጻ ድርጅቶች የሉትም። ኢህአዴግ አድርባይ ባለስልጣናት እንጂ ነጻ አመራሮች የሉትም። ሁሉም አድርባዮች ተጠሪነታቸው ለህወሃት ስለሆነ ተጠያቂውም ራሱ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት እንጂ ሌሎች ሊሆኑ አይገባም። “ፈጣሪያቸው” የሚገመግማቸው፣ እነሱም አምነው የሚገመገሙት ታማኝ አድርባይ ስለሆኑ ብቻ ነው።
አሁን እየተለመደ የመጣው የመፈክርና የቀረርቶ ጉዳይ አጥወልውሎ የሚጥል ደረጃ ያደረሰንም ለዚህ ነው። ቃላት ማምረትና ማራባት የተካነበት ኢህአዴግ በየጊዜው የሚፈለፍላቸው ቃላቶች እያንገፈገፉን ነው። በተለይም ታላላቅ ዋጋ ባላቸው “ውድ” ቃላቶች ላይ አደጋ እየፈጠረም እንደሆነ ይሰማናል፤ ይጫወትባቸዋል። አድርባይ ሚዲያዎችና አድርባይ ጋዜጠኞች የማከፋፈሉን ስራ ይሰራሉ። ይህ በአገር ደረጃ የተንሰራፋው አድርባይነት ለኢህአዴግ ስጋቱ አይደለም፤ ኩራቱ እንጂ!!
ይህንን ያነሳነው ወድደን አይደለም። ባለፈው ሳምንት ባወጣነው የአባይ ግድብ ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም የሚል ዜና አድርባይ እንድንሆን ያሳሰቡን በመኖራቸው ነው። ስለ አባይ ግድብ ያሰራጨነው ዜና ያስደነገጣቸው በርካቶች ናቸው። የአባይ ግድብ መገደብ እውን መሆን አለበት። አባይ ተገድቦ አገር መልማት አለበት። አባይን ለልማት ለመጠቀም ለሚገጥም ችግር ሁሉ ሁላችንም “ልዩነት” ሳይገድበን ዘብ እንቆማለን!! ግን የግልጽነት ጥያቄ ያሳስበናል። ያስጨንቀናል። “በልማትና ዕድገት” ስም የተድበሰበሱ ውሎችና ስምምነቶች እኛንም ሆነ መጪውን ትውልድ ዋጋ እንዳያስከፍሉን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ እናምናለን። በዚህ ጉዳይ ላይ አድርባይነት የለም!!

Saturday, May 18, 2013

ብርሃንና ሰላም በህገ ወጥ መንገድ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣን አላትምም ማለቱ ሕገ ወጥ ነው


የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ልሳን የሆነችው እና በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የነፃ ጋዜጦችን መታፈን፣ መመናመን እና ድፍረት ማጣት ተከትሎ ዘወትር ማክሰኞ ጠንካራ የፖለቲካ ትንታኔዎችንና ዜናዎችን በመያዝ ለህትመት የምትበቃው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ብርሃንና ሰላም የህግ አግባብ በሌለው ውሳኔ አላትምም ማለቱ ህገ ወጥ በመሆኑ በአስቸኩዋይ ይታረም ሲል የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አስታወቀ፡፡
     ለህትመት ከበቃችበት ጊዜ ጀምሮ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን በማትረፍ ተናፋቂ ለመሆን የበቃችው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንዳትታተም በብርሃንና ሰላም የታገደችበት ሁኔታ ከጠ/ሚ መለስ ሞት ጋር የሚያያዝ ሲሆን ጋዜጣዋ የፖቲካ ፓርቲ ልሳን እንደመሆንዋና ፓርቲው ደግሞ ያለበትን ሃገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት የጠቅላይ ሚንስትሩን ሞት ተከትሎ በሃገሪቱ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ምን መልክ እንደሚኖራቸው የሚያሳይ የፖለቲካ አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የጋዜጣዋ ክፍል ባልደረቦች የፃፉዋቸውን ትንታኔዎች በልዩ ዕትም ዓርብ ነሐሴ 18 ቀን 2004 ዓ.ም ለንባብ ማብቃቱ የሚታወስ ነው፡፡ በመቀጠልም ማክሰኞ በመደበኛ ቀንዋ ጋዜጣዋ ለአንባቢያን የደረሰች ሲሆን፡፡ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ ጠንካራ ሃሳብ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ለማስተናገድ እንደገና ዓርብ ነሐሴ 25 ቀን 2004 ዓ.ም  የጋዜጣ ክፍሉ በመረባረብ ስራውን አጠናቆ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ እንደተለመደው ገንዘብ ለመክፈል የህትመት ክትትል ሰራኛው ሲሄድ እንዳይታተም ታግዷል በማለት መልሰውታል፡፡
     የህዝብ ግንኙነትቱ አያይዞ እንደገለፀው አቶ መኮንን አበራ የተባሉትን የማርኬቲንግ ማናጀርና ከአገዱት የማኔጅመንት አባል አንዱ የሆኑትን ጠይቆ እንደተረዳው ‹‹ጋዜጣው የጠ/ሚ መለስን ሞት ተከትሎ የወጡ ፅሁፎች ጥሩ አልነበሩም ህዝቡም አስተያየት ሰጥቶናል››  ከማለት ውጭ የትኛው ዘገባ ጥሩ እናዳልነበር የገለፁት ነገር የለም፡፡ እገዳውም በወረቀት ሳይሆን በቃል ነው፡፡ እገዳውን የፈፀሙትም የማተሚያ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት ከህግ አግባብ ውጭ ነው፡፡
    የህዝብ ግንኙነት ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ተፈራ ስለጉዳዩ ሲገልፁ ‹‹እኛ በህጋዊ መንገድ የምንንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነን፡፡ የሃገራችን ጉዳይ ያሳስበናል፣ የህዝቡ ጉዳይ ያሳስበናል፣ የሉዓላዊነታችን ጉዳይ ያሳስበናል እንዲሁም የአቶ መለስ ድንገተኛ ሞትና ተከታዩ ጊዜ ያሳስበናል ስለዚህ ያወጣናቸው ዘገባዎች አግባብነት ያላቸውና ወቅታዊ ነበሩ፡፡ አቶ መለስ መሞታቸውን እንደሰማንም የሃዘን መግለጫ በማውጣት የተሰማንን ሀዘን ገልጠናል፡፡ ከዚህ በላይ ግን የሚያሳስበን የሀገራችን ዱዳይ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡
    በቀጣይም አገዱ የተባሉትን የማኔጅመንት አካላት ለማነጋገር የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ቀጠሮ የያዙ ሲሆን እገዳው ህገ-ወጥ በመሆኑ እስከ መጨረሻው የምንታገለው ይሆናል፡፡ ከህዝብ ጋር የመገናኛ በራችንን ሲዘጉ ዝም ብለን አንመለከትም፡፡ ከዚያ በፊት ግን የማተሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ስህተታቸውን ያርማሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ በማለት የአንድነት  የህዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡