Tuesday, November 19, 2013

23 ዓመት የተገነባ የበደል ውጤት ።

ወያኔ ኢትዬጵያዊነትን ትርጉም ኣልባ ለማድረግ ገና ከመነሻው፣ ከጥንስሱ አስከዛሬዋ ቀን ድረስ የክፋትን ድር ኣያደራ ፣የሚፈራውን አያስፈራራ፣አያሰረ፣አየገደለ፣አያሳደደ ወዘተ ዜጎች በሀገራቸው ላይ ባሪያ ሆነወ አንዲኖሩ አያፈነ ኢትዬፒያዊ ጀግንነት እና የኢትዬጵያን ክብር የትላነት ታሪከ አነዲሆነ አየጣረ ነው ዛሬ ዛሬ ኢትዬጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር የሚለውን ኣባባል ስሰማ ውሰጤ ትልቅ ጥያቄ ይፈጠራል አውነት ዛሬ ሀገራችን ከነክብርዋ ኣለች ? ኣባቶች ወኔኣቸው ጠፍቶ ለዝምታ አጅ ከሰጡ አናቶች ፍት በማጣት ኣንገታቸውን ከደፉ ኣህቶች የሴትነት ክብራቸው ተገፎ ለኣረብ መጫወቻነት ከተሸጡ ኣንድ ትውልድ አውነት ሳይሰማ ካድገ ፣ገበሬው ማረሻው ተነጥቆ አጆቹ ለልመና ከተዘረጉ የኢትዮጵያን ክብር የምናየው ማን ላይ ነው ፣ዘላለማዊት ኢትዮጵያን የምንመኘው ለየትኛው ትውልድ ነው ?
 በወያኔ የኣገዛዘ ዘመን ሀገራችን ላይ ችግሮች መልካቸውን አየቅያየሩ ህዝቡን ሲደቁሱት ኖረዋል ዛሬም አያየነው ነው
የዘረ ማጥፋት ወንጀል፣
 ዜጎች በኣደባባይ በግፍ መገደል፣
 የተቃዋሚ ፓርቲ ኣባላት ፣ደጋፊዎቻቸው አና ጋዜጠኞች ያለፍት መታሰር
 ነዋሪዎች ከቀዬኣቸው መፈናቀል.... ወዘተ አነዚህ አና የመሳሰሉ ሀገራችን ላይ የሚፈጸሙት ግፎች ሰሞነኛ ወሬ ሆነው ሳይፈቱ አስከዛሬ ኣሉ ፣ዛሬም ወገኖቻችን ላይ በኣረብ ሀገራት አየደረሰ ያለው ስቃይ አና አንግልት ወያኔ ለዜጎች አና ለሀገራችን ያለው ንቅት የወለደው ነው (ባለቤት የናቀው ኣሞሌ........ ) አንዲሉ ኢትዮጵያዊነት አንደወንል የሚቅጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰን ወገኖቻችን የወያኔን የግፍ ጅራፍ ሸሽተው በተሰደዱ በባአደ ሀገራት አስር ቤት ታጉረው በየኣደባባዩ ሬሳቸው ወድቆ ደማቸው ደመከለብ ሆኖዋል
 በወያኔ ኣገዛዝ የሰረኣቱ ዋነኛ ተጎጂ የሆኑት ሴቶች ናቸው በ1000 የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ለጉለበት ስራ በህገወጥ መንገድ ወደኣረብ ሀገራት ይሰደዳሉ በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ አንዳይችሉ በመንገስት ኣካላት የሚደርሰባቸው የሰባዊ መብተ ረገጣ መፍትሄ ማጣት አና የጭቆናው ምሬት ስደት ብቻኛ ምርጫቸው አንዲሆን ያስገድ ዳቸዋል አብዛኞቹ ኣድሜኣቸው ከ18 በታች የሆኑ ህጻናት ከኣቅም በላይ በሆነ ያጉልበት ስራ በቀን 18 ሰዓት በላይ አንዲሰሩ ይገደዳሉ ፣በኣሰሪዎቻቸው በተደጋጋሚ ይደፈራሉ፣ ይደበደባሉ ይገደላሉ የሚደርስባቸው ስቃይ ከኣቅማቸው በላይ የሆነባቸው ብዙዎች ለኣይምሮ ችግር ተዳርገው በየጎዳናው ወድቀዋል ሰሚ ያጡ ዋይታዎች ፣ድብደባ መቛቛም ያቃታቸው በመደፈር ብዛት የደከሙ የጨቅላ ገላዎች በደል የበዛባቸው ብዙ አህቶች አራሳቸውን ከፎቅ በመወርወር መርዝ በመጠጣት በመታነቅ ሂወታቸውን ያጠፋሉ።
ይህ ሁሉ የአንድ ቀን ምሬት ፣የ አንድ ሰሞን ብስጭት የፈጠረው አይደለም 23 ዓመት የተገነባ የበደል ውጤት ነው ። 

Monday, November 18, 2013

“Remember, the Ethiopian Martyrs of June and November, 2005 Forever!”

Ethiopia: I Always Remember in November and in…

November 17, 2013
Ethiopian parliamentary elections in May 2005
For Ethiopians, November is a month which shall live in infamy
In November 2013, Ethiopians in Saudi Arabia are facing unspeakable horrors.
For the past few years, there has been systematic persecution of Ethiopians living, working and seeking refuge in Saudi Arabia. Even Ethiopians practicing their faith in the complete privacy of their homes have faced criminal prosecution and deportation. In 2011, according to a Human Rights Watch report, Saudi police arrested “thirty five Ethiopian Christians for ‘illicit mingling,’” while the  “Ethiopians gathered to pray together during the advent of Christmas, in the private home of one of the Ethiopians.”
It is no exaggeration to say it is open season on Ethiopian migrant workers and others seeking refuge in Saudi Arabia. Every day this month, Saudi police, security officials and ordinary Saudis have been hunting Ethiopians in the streets, beating, torturing and in some cases killing them. The video clips of Saudi police torturing Ethiopians are shocking to the conscience. The  video clips of Saudi mobs chasing, attacking and lynching Ethiopians in the streets requires no explanation. The photographs of crimes against humanity committed against Ethiopians in Saudi Arabia today are surreal and beyond civilized comprehension!!!
What is the regime in Ethiopia doing to help the estimated 200,000 plus Ethiopians in Saudi Arabia? Not a damn thing!
By its own admission, the regime has no idea how many Ethiopians are living in Saudi Arabia, but ludicrously promises to bring them all back “as soon as possible.”  The malaria researcher-turned-“foreign minister”, Tedros Adhanom, blathered that his regime “has condemned Saudi Arabia for its brutal crackdown on migrant workers in the kingdom. This is unacceptable. We call on the Saudi government to investigate this issue seriously. We are also happy to take our citizens, who should be treated with dignity while they are there.” “Unacceptable” is the most condemnatory language the regime could muster in the face of such monstrous cruelty, unspeakable barbarism and horrendous brutality and criminality.Al Jazeera reported that when outraged Ethiopians sought to peacefully protest in front of the Saudi embassy in Addis Ababa, they were arrested and beaten by regime policemen. “‘The police came and they beat us…and now more than 100 people are at the police station,” said Getaneh Balcha, a senior member of the opposition Blue Party movement, adding the party chairman and vice chairman were among those held.’” But should we really be surprised because…

Sunday, November 17, 2013

ወገን አልባው ወገን , ጠባቂ አልባው ግልገል


ወገኔ በከንቱ

saudi ethio8
እዩት በየቦታው የሚታደገው አጥቶ
እንዲያው ሲንከራተት ከሀገሩ ወጥቶ
ወይ አላለፈለት ወይ እፎይ አላለ
ሁሌ በባርነት እንዲሁ እንደቆዘመ
ዘመናዊ ለማኝ አስጠጉኝ ባይ ሆነ
መገፋቱ ሳያንስ መገደሉ ባሰ ።
ባርነት ባአረብ አገር
እስር በዐገር ቤት
ስደት ካገር ውጭ
ችግር በራስ አገር
እርዛት አና እስር
ሆኖል የብሶት መንደር ።
ወገን አልባው ወገን
ጠባቂ አልባው ግልገል
መንጋው ተበተነ ዋይታው ለኛ ሆነ
ገዳዩም ጠያቂ አጣ ስቃዩም ቀጠለ ።
አቤት ፍርጃ ለዛውም ጠያቂ ያጣ
ምን ይሆን ሚስጥሩ እንዲህ የመሆኑ?
ማብቂያውስ መቸ ነው እንግልት ስደቱ
አገር ሰላም ሆኖ ሰርቶ እሚኖርበት ሁሉም አንደቤቱ።
መንግስት ምን አገባኝ ጆሮ ዳባ ልበስ ካለ
ለህዝብ ለወገኑ ላገሩ ካልቆመ
የወገን ደም እንደቀለም መንገድ ላይ ሲዘራ
በባእዳን እጂ ወገን ሲሆን መቀለጃ
ቆሞ ተመልካች ሙሾ አውራጂ ብቻ
አውጋዥ ማን አረገው ጥቃት ተከላካይ አንጂ
መንጋውን ከቀበሮ ከፍየል እጂ ።
ዳሩ ምን ያደርጋል አሳዳጁ ማን ሆነና
የችግሩ መንስኤ ገፊ እና አስገዳጂ
ዘር ከገበሬ ነጥቆ መሬት ሻጭ
ከገዛ አገር ኣፈናቃይ ሰርቶ እንዳይበላ
ሰርቶ አደር ገዳይ ፍት ህን አጉዳይ
ለነጻነት ታጋይን አሸባሪ ባይ
አሳሪና ገዳይ እንዲሁም ቆሞ አስገዳይ።
ይሀው ነው ውጤቱ መንግስት ያለቦታው
ያለህዝብ ምርጫ ስልጣን ላይ መውጣቱ
ለህግ ሳይገዙ  በህግ ስበብ ህዝብን ማሸበሩ ።
ይሁና የምንልበት ጊዜ አብቅቶል
የወገን ደም ያለ አግባብ ፈሶል
ተነሱ እንነሳ ድምጻችንን አናሰማ
ላለቀው ወገናችን ላለው በሰቆቃ
ደግሞም እንጩህ ወደፈጣሪያችን
አይቶ ወደሚምረው ወደ አምላካችን።
ከምስራቅ መንበሩ
 http://www.goolgule.com/my-people/

Tuesday, November 5, 2013

Ethiopia arrests 2 journalists from independent paper (CPJ)

Ethiopia arrests 2 journalists from independent paper

Getachew Worku is being held without charge. (Ethio-Mihdar)
Getachew Worku is being held without charge. (Ethio-Mihdar)
New York, November 5, 2013--Ethiopian police have arrested without charge two editors of the leading independent Amharic weekly Ethio-Mihdar, according to local journalists.
Police in the town of Legetafo, northeast of the capital Addis Ababa, on Monday arrested Getachew Worku in connection a story published in October alleging corruption in the town administration, according to Muluken Tesfaw, a reporter with the paper, who spoke to Getachew shortly after his arrest. Getachew has not been charged, he said.
On Saturday, police arrested Million Degnew, the general manager of the newspaper, and Muna Ahmedin, a secretary, said Muluken and local journalists. Muna was released the same day but Million remains in custody without charge, Muluken said.
"A free and inquisitive media is a cornerstone of development that should benefit all Ethiopians," said CPJ's Africa Program Coordinator Sue Valentine. "Repeatedly detaining journalists without charge is an intimidation tactic that must end. We urge the authorities to release Million Degnew and Getachew Worku immediately."
The government has harassed Ethio-Mihdar in the past for its independent coverage, according to CPJ research. Million and Getachew have been sued for defamation by the public Hawassa University, according to local journalists and news reports. University officials are seeking 300,000 birr (US$15,000) and the closure of the newspaper over a report alleging corruption in the school's administration, according to local journalists.
In May, Muluken was detained for 10 days while reporting on evictions of farmers from their land in northwest Ethiopia. He was released without charge.
Ethiopia trails only Eritrea as Africa's worst jailer of journalists, according to CPJ's annualprison census. More than 75 publications have been forced to close under government pressure since 1993, CPJ research shows.

source: CPJ (Committee to Protect Journalist)

Monday, November 4, 2013

አለም ይቁጠረው የኢትዮጲያን ስደት እና ሞት


አኔ እምለው በቃ እንዲሁ ሆነ ያገሬ ሰው አጣ ፈንታው በወያኔ የግዞት አመራር? ባገር ውስጥ የሚፈጥጽመው ግፍ አገዛዝ፤ ስቃይ እና እስሩ አልበቃ ብሎት፣ ህገወጥ የሰው ንግድ ዝውውር ለውጭ ምንዛሬ ሲባል ከእለት ተለት፤ ከአመት አመት እየባሰ መጥቶ ጭራሽ የየቀኑ ውሎዋችን ዜና ሆነና አረፈው።

Bloomberg የተባለ የዜና ድህረ ገጽ እንደዘገበው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ 2012 አመተ ምህረት 160,000 የሚሆኑ ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ የባርነት ንግድ ወይም የጉልበት ስራ ወደ ሳውዲ አረቢያ ተጉዘዋል ፤በቅርቡ አየሰማናቸው ካሉት የሴት እህቶቻችን የስቅላት አና የሞት አንዲሁም የስቃይ ዜናዋች ከነዚሁ ውስጥ ይገኙበታል ማለት ነው።

 Gulf Arab states በሚባሉት የአረብ ሀገራት Kuwait, Bahrain, saudi Arabia, United Arab Emirates በመሳሰሉት ሀገሮች ከኢትዮጲያ ወደነዚህ ሀገራት በቀን 1500 የሚሆኑ ወገኖቻችን ለጉልበት ስራ እንደሚሰደዱ UPPSALA UNIVERSITY  June 2013 ለጥናት ምርምር ባቀረበው ጽሁፉ ላይ ገልጾል።


አጂጉን የሚያሳዝነው ነገር እነዚሁ ወገኖቻችን አገር ወገን ተቆርቆሪ እንደሌለው ባሰሪዋቻቸው ስቃይ እና በደል፤ መደፈር፤ ግርፋት፥ አንዲሁም ሰቀላ እንኩዋን ሲደርስባቸው በዛው አገር የሚገኘው የይስሙላ ኢትዮጲያ ኤምባሲ ኡኡ የድረሱልን ጥሪ እንኩዋን ሲባሉ ወግ ሆኖ እንኵዋ የዜጎችን መብት ሊያስከብር አና በህግ ሊጠይቅ ቀርቶ ባልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ቆሞ አስጨፍጫፊ ሆኑዋል።

ህግ አርቃቂ እና አውጭ ነገር ግን መተግበር አላርጂኩ የሆነው ዬኢትዮጲያ መንግስት በመተዳደሪያ ህገመንግስቱ ላይ ህገወጥ የሰው ንግድ ዝውውርን ሲፍጽም የተገኘ ከአምስት እስከ ሃያ አመት የእስር ቅጣት እንደሚያገኘው የደነገገ ሲሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግን መንግስት የዚሁ ህገወጥ የሰው ዝውውር ንግድ እረጂና ፈጽሚ ነው። ለምን ሲባል ለውጭ ምንዛሬ !

አፍንጫው ስር ሆነው የህጻናት፥የሴት አና የወንድሞቻችን ሀገወጥ የሰው ንግድ ዝውውር ገበያ የሚገበያዩትን ኤጀንሲዋች አላየሁም ቢል መሳቂያ ከመሆን አልፎ ,በጎንም እነዚሁን ዔጀንሲዋች እንደሚረዳ ግልጽ ነው። የወገኖቻችን ስቃይ አና ሞታቸው አፍጥጦ እንዲህ የሚዲያዎች ሁሉ መወያያ ሲሆን ግን ያው የተለመደ ፕሮፓጋንዳ ግድ ነው። አስቁመናል፤ አስረናል፤ ቀጥተናል ወዘተ፤ የስደቱስ ምንጬ ማቆሚያው ምንድን ነው?  ወገኖቻችን ያለውን ስቃይ አና በደል እየሰሙ ፤እያዩስ አገራችው መኖር ከዛው ስቃይ ያለተናነሰ መሆኑን አይተው መርጠው የወጡት ለምንድነው?   በባህር ፤ በበረሃ እንደዘበት በሞት እየቀሩ ፤ከተወለዱበት አገር ከተከፈሉበት ዘመድ እና ወገን አልባ ሆነው የቀሩት ለምን የሆን?  እንግዲህ አለም ይቁጠረው!

ሌላው በጣም የሚያሳዝነው እና ልብ የሚሰብረው ጉዳይ የሴት እህቶቻችን ስቃይ እና ጥቃት በባእዳን አገር አና ወገን ብቻ ሳይሆን ባገራቸው ላይ በገዥው መንግስት ባለስልጣናት እና ታጣቂ ወታደሮችም መሆኑም ጭምር ነው። allAfrica የተባለ የዜና ደህረ ገጽ እንደዘገበው በ 2011 February   በኦጋዴን የሚገኙ የኢትዮጲያ ሶማሌ ሴት እህቶቻችንን የኦጋዴን ነጻ አውጭ(ONLF) ደግፋችዋል በማለት በዔሌክትሪክ ሾክ በማሰቃየት፤ በእሳት በመጥበስ አንዲሁም በእስር ስቃይ የተፈጸመባችውን የሴት እህቶቻችንን ስቃይ ከፎቶ ማስረጃ ጋር በተደገፈ አቅርቦል።

መቸስ ሌላው ሌላውን በደል እና ስቃይ እንዲሁም የመንግስት አፈና ቤት ይቁጠረው ብለን ነው። ያዲስ አበባ እስር ቤቶች ፤ማእከላዊ እና ቃሊቲ፤ አንዲሁም ሌሎች የየክፍለሃገር እስር ቤቶች ያጎሩትን ፤ ቤት ይቁጠረው ነው።


http://allafrica.com/view/photoessay/user/user/id/201102100001.html
http://www.youtube.com/watch?v=ZvuErWmFw3I




Sunday, November 3, 2013

የድሬዳዋ ከተማ በጉንፋን መልክ በሚከሰት የበሽታ ወረርሽኝ ሥጋት ላይ ነች በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ የራስ ምታት፣ ማንቀጥቀጥና ነስር እንደሚታይባቸውና ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ በጉንፋን መልክ በሚከሰት የበሽታ ወረርሽኝ ሥጋት ላይ ነች፡፡ በዚህ ወር ብቻ በበሽታው የተያዙ 2ሺ ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡
ከወባ ጋር ተመሣሣይነት አለው በተባለው በዚህ በሽታ የተያዙ ህሙማን፣ በድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታልና በተለያዩ የከተማዋ ክሊኒኮችና የጤና ተቋማት ምርመራና ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ በበሽታው ተይዘው ህይወታቸው ያለፈ ህሙማን እንዳሉ ምንጮች ቢጠቁሙም፤ የከተማው ጤና ቢሮ ለሞት የተዳረጉ ህሙማን መኖራቸውን አላውቅም ብሏል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ካሣሁን ኃ/ጊዮርጊስን ስለ ጉዳዩ ጠይቀናቸው፤ ችግሩ ወረርሽኝ በሚባል ደርጃ ተከስቷል ለማለት እንደማይቻልና ገና ስለሁኔታው ማጣራት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ የወባ በሽታ የሚስፋፋበት ወቅት ከመሆኑ አንፃር በአካባቢው ጠበቅ ያለ ዝግጅትና ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ካሣሁን፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ከወትሮው የተለየ ቁጥር ያላቸው ህሙማን መመዝገብ መቻላቸው ሁኔታውን ትኩረት እንድንሰጥበት አስገድዶናል ብለዋል፡፡
በዚህ ወር ብቻ 2ሺ ሰዎች መመዝገባቸውንም አቶ ካሣሁን ተናግረዋል፡፡ የበሽታውን ምንነትና የመተላለፊያ መንገዱን ለማወቅ ናሙናውን ወደ አዲስ አበባ የጤናና ሥነ-ምግብ ምርምር ኢንስቲቲዩት (ፓስተር) መላኩንና ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የበሽታው ምንነት ባልታወቀበት ሁኔታ ግን ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገሩም አቶ ካሳሁን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ሁኔታውን አስመልክቶ የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በየዕለቱ ወደ ፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እየላኩ መሆናውን እና የበሽታውን ምንነትና የመተላለፊያ መንገዱን በቀጣዩ ሳምንት መረጃው ተጠናቆ እንደደረሳቸው ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ከሸንሌና ሔረር ተነስቶ ወደ ከተማዋ ተዛምቷል የሚል ጥርጣሬ ባሳደረው በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ የራስ ምታት፣ ማንቀጥቀጥና ነስር እንደሚታይባቸውና በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የሚታየው ከፍተኛ ሙቀት ለችግሩ መፍጠር ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸውም ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡