Monday, May 13, 2013

የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት መብቶች በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም (በተለይ ለዞን 9)


Prof. Mesfin Woldemariam በሥራ ላይ አለ የሚባለው በ1987 ዓ.ም. የወጣው ሕገ መንግሥት አንቀጽ 30ና 31 የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት፣ የመደራጀት መብት ይደነግጋሉ፤ ነገር ግን ሁለቱም አንቀጾች ግን እያሉ መፍረሻውን ወይም ማርከሻውን አብረው ይገልጻሉ፤ እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው ነው፡ይህ ዘዴ በአጼ ኃይለ ሥላሴም ሆነ በደርግ ሕገ መንግሥቶች ውስጥ የሚታይ ነበር፡፡
የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት መብቶች የሕዝቡን ስሜትና ፈቃድ ለማወቅ ለሚፈልግ መንግሥት የእነዚህ መብቶች በተግባር መዋል በጣም ፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም መንግሥትንና ሕዝብን ያቀራርባሉ፤ የእነዚህ መብቶች መታፈን የሚያሳየው በመንግሥት ፋንታ አገዛዝ መኖሩንና ሕዝቡን ያለፈቃዱ በኃይል ብቻ የሚገዛ መሆኑን ነው፡፡
አንቀጽ 30‹‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፤›› ከአለ በኋላ ‹‹ዴሞክራሲያዊ መብቶችንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ፤›› በማለት የአንቀጹን ዋና ርእስ ያደበዝዘዋል፤ ያውም ምንም ትርጉም በሌለው ማመካኛ ነው፤ እግዚአብሔር ያሳያችሁ መሠረታዊ የሆነ የዴሞክራሲ ማሙያዎች የሆኑትን የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍን የማድረግ መብት ‹‹ዴሞክራሲያዊ መብቶችንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ እንዳይጥሱ›› በሚል በተምታታና ግልጽ ባልሆነ አስተሳሰብ ዋናውን መብት ለመገደብ ‹‹ሕጋዊ›› የሚመስል ማመካኛ ፈጠሩ፤ በዚህም ምክንያት በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ የሚመስሉት አንቀጾች በተግባር ታግተዋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመሰብሰብም ሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መትረየስንና ክላሽን የሚጋርድና የሚከላከል ጥላ ያስፈልጋል፤ አነዚህ የሕገ መንግሥቱ አንቀጾች ከሥራ ውጭ በመሆናቸው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበርና የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ወደአለመኖር ተሸጋግረዋል፡፡
አሁን ደግሞ በፖሊቲካ ፓርቲዎች ላይ ጭቆናውና አፈናው እየበረታ በመሄዱ ፖሊቲካ ፓርቲዎች ሕዝባዊ ስብሰባ የሚያደርጉበት አዳራሽ (የግልም ሆነ የመንግሥት) ማግኘት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ በሰላማዊ ሰልፍም አገዛዙ መሳቂያና መሳለቂያ ሆኖአል፤ ለግራዚያኒ በኢጣልያ የሚሠራውን ሐውልት ለመቃወም ጥቂት ዜጎች በስድስት ኪሎ ቢሰበሰቡ ፖሊሶችና የደኅንነት ነጭ ለባሾች እየደበደቡ ይዘው፣ አንድ ቀን አስረው በበነጋታው በዋስ ለቀዋቸዋል፤ በፋሺስት ኢጣልያ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ካልተፈቀደ ለምን ይፈቀዳል?በዚህ ሁሉ ላይ ጋዜጠኞችን ሽብርተኞች እያሉ ወደወህኒ ቤት በመወርወር ጋዜጠኞች ሁሉ አንድም ወደስደት አንድም ወደወህኒ እየገቡ ነጻ ጋዜጣ እየጠፋ ነው፤ ስለዚህም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለገብ አፈና ሰፍኖአል ለማለት ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ሕዝቡ ቤቱ ሲፈርስ፣ መሬቱን ሲነጠቅ፣ ከኑሮው እየተፈናቀለ ሲባረር፣ ፍትሕ ሲጠፋ፣ ክብሩንና ኩራተን ተገፎ በያገሩ ሲሰደድና ውርደት ሲደርስበት ተሰብስቦ ለመወያየት መብት የለውም፤ በተናጠል እንባውን እያፈሰሰ ወደአምላኩ ማመልከት ልማድ ሆኖአል፤ በአገዛዙ ወንበር ላይ የተቀመጡት እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ሕዝብ ግፍ የማያይ፣ ጩኸቱንም የማይሰማ ይመስላቸዋል፤ አግዚአብሔር ግን ሁሉንም ይመዘግባል፤ ለንስሐ የሰጣቸው ጊዜ ሲያበቃ ፍርዱን ለእያንዳንዱ ይሰጣል፤ ያን ጊዜ ኃይልም፣ ሀብትም፣ ሥልጣንም የሕዝብ ይሆናል፡፡

የአቶ ገብረዋህድ ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአቶ ገብረዋህድ ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ባለቤት ኮሎኔል 
ሃይማኖት ተስፋይ ባለቤታቸው ከተጠረጠሩት ወንጀል ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶችን ሲያሸሹ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከፖሊስ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ኮሎኔል ሃይማኖት ከመኖሪያ ቤታቸው ወስደው በሌሎች ግለሰቦች እጅ እንዲደበቁ ያሸሻቸው ሰነዶች በተለያዩ ቦታዎች በአቶ ገብረዋህድ ስም የተመዘገቡ የቤትና የቦታ ካርታዎች ናቸው፡፡
ኮሎኔል ሃይማኖት ካርታዎችን ሲያሸሹ ጥቆማ የደረሳቸው የደህንነትና የፖሊስ ሃይሎችም ክትትል በማድረግ ካርታዎቹን ከተደበቁበት ቦታ ይዘዋቸዋል፡፡
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ግንቦት 2/ 2005 በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ቤት በተደረገው ብርበራ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያና የውጭ ሃገራት ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶች መገኘታቸው ይታወሳል፡፡ 

Monday, March 4, 2013

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!



በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)
ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን  የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ  ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡
ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን  በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና  የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ  የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ  በፍቅር አብረን ኑረናል፤  የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡
እንዴት እንደ  ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ  ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6316

Saturday, March 2, 2013

ተጋዳይ ማትያስ ሹመት ያዳብር

ተጋዳይ ማትያስ ሹመት ያዳብርእንዳይነቀሳቀስ አጁን በስንሰለት ጠፍረህ አሰረኸው፡ሽጉጥክን ደግነህ ተናዘዝ ብትለው፡
በእምነቴ አትምጣ ከፈለክ ያውልህ ደረቴን ለጥይት፡
ደጀ ሰላም ከወራት በፊት አቡነ ማትያስ እንደሚሾሙ ያሳወቀችው እውን ሆኗል፤ከቶ አልበገርም በባዶ ድራማ አድማጭ የለሽ ተረት፡
ሞቴን ከነምነቴ ብሎ በመጽናቱ ግራ የተጋባህ፡
ደንባራ ወያኔ ፊልም መቆራረጥ መቀጣጠል ገባህ፡፡
አንተ አቡ በከር አንድ ጎኔን ሞቀው በጣም አኮራኸኝ ፡
አኩል አልሞቅ አለኝ አንዱ ጎኔ ሳስቶ ክፉኛ በረደኝ ።
እንኳንስ ተከታይ፤ አስተማሪው ካህን መነኩሴው ጳጳሱ፡
ለምነት አለቆም አለ አሳሳችው ነፍሱ።
ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መሆኗ ቀረና የእምነት ማህደር፡
ታጋይ ተፈራርቆ ይሾምባት ጀመር።
የሃይማኖት መሪ በግዜር ይመረጣል ተብይ አድጌ፡
አገር በጾም ጸሎት ትጸናለች ሲባል ተምሬ አድጌ፤
ታጋይ ጳጳስ ሲሆን ስተቱ የማን ነው? መልስ አጣሁ ፈልጌ።
በመርዝ በጥይት ወገኑን ጨርሶ የመጣ ሹመኛ ደብሩን ቢረከበው፡
እግዜር የሾመው ነው በሚል አጉል ባህል መስቀል ልሳለም ነው?
ወይስ
አንት እርኩስ መንፈስ ተጣልቼሃለሁ፡
መስቀልህ ይቅርብኝ ቤቴ ጸልያለሁ፡
ገንዘቤም በኪሴ ለምን ጦርሃለሁ፡
ብዬ ላሳርፈው?
ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን የምትሆነው ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው የሃይማኖት መሪ ሲኖራት እንጂ የፖለቲካ ስልጣን በተቆጣጠሩ ባለስልጣናት የሚሾም ካድሬ ቁጥጥር ስር ሆና አደለም ፡ ስለዚህ ለተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ ማስተላለፍ የምፈልገው ምልእክት፡ ስርዓት እሰኪከበር ድረስ ጸሎታችሁን በቤታችሁ ገንዘባችሁን በኪሳችሁ እንድታረጉት እንዲሆን ነው፡ በገዛ ገንዘባችሁ ወያኔን የምታዳብሩበት ምክንያት አይኖርም፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
እስከ ነጻነት