ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ።
መንግስት በሃይማኖታዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ መግባቱን የተቃወሙ ሙስሊሞች ዓመቱን ሙሉ በጸጥታ ሃይሎች የዘፈቀደ እስር፣ እገታ፣ ድብደባ እና ሌሎች ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. የታሰሩት 29ኙ የተቃውሞው መሪዎች የፍርድ ሂደት ከጥር ወር 2013 ጀምሮ ለህዝብ፣ ለመገናኛ ብዙሃን፣ እና ለቤተሰብ አባላት ዝግ ተደርጓል፡፡ እጅግ አወዛጋቢና መሠረታዊ ግድፈት ያለባቸውን ድንጋጌዎች በያዘው የሃገሪቱ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ መሰረት ጥፋተኛ የተባሉ የተቃዋሚ መሪዎች እንዲሁም አራት ጋዜጠኞች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
ከሃገር ውስጥ በሚገኝ ገቢ እና ከውጭ በሚመጣ እርዳታ በሚደገፉ ስፋት ያላቸው የልማት ፕሮግራሞች አፈጻጸም ምክንያት የአንዳንድ ማህበረሰብ ተወላጅ ነዋሪዎች ያለበቂ ምክክር ወይም ምንም አይነት ካሳ ሳይከፈላቸው ከመኖርያቸው እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው አንስተው ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር ሃይል፣ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይፈጸማሉ፤ ለምሳሌ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የሚገኙ ተወላጅ ነዋሪዎች ለዘመናት የኖሩበት መሬት መንግስት ለሚያካሂደው የስኳር መስኖ ልማት ይፈለጋል በሚል መፈናቀላቸው እንደቀጠለ ነው።
በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት
ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር የሚይዙት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞ አድርገዋል፡፡ የተቃውሞው መነሻ ምክንያት መንግስት በእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ውስጥ እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የአወሊያ መስጊድ ላይ ይፈጽማል የተባለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ነው፡፡
የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹን ለመግታት መንግስት ሃይል ተጠቅሟል፤ የዘፈቀደ እስር እና ድብደባ በተቃዋሚዎቹ ላይ ፈጽሟል፤ እነዚህ ሕገ ወጥ ተግባራት በሀምሌ 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው በጥቅምት 2012 ዓ.ም በጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት ክስ በተመሰረተባቸው 29 ታዋቂ የተቃውሞ እንቅስቃሴው መሪዎች ላይም ተፈጽመዋል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደቱን መገናኛ ብዙሃንን፣ ዲፕሎማቶችን እና የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ህዝብ እንዳይከታተለው ከጥር ወር ጀምሮ ዝግ አድርጎታል፡፡ አንዳንዶቹ ተከሳሾች በእስር ላይ እያሉ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል። እንዲሁም እንዳንዶቹ ተከሳሾች ለሁለት ወራት ያህል የሕግ አማካሪ ወይም ጠበቃ ያላገኙበት ሁኔታና ከቤተዘመድ ጋር ለመገናኘት የነበረውን ችግር ጨምሮ የፍርድ ሂደቱ በሕግ በተቀመጡ ስርዓቶች አግባብ መካሄዱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ በርካታ ግድፈቶች ተፈጽመዋል.........
more...... http://www.hrw.org/world-report/2014/country-chapters/121939
Women and Politics in Ethiopia
Tuesday, January 21, 2014
Monday, January 6, 2014
“አንድነት” የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምፅ ማግኘቱን ገለፀ::
የፀረ-ሽብር አዋጁን በመቃወም “የሚሊዮኖች ድምፅ” በሚል መርሃግብር የህዝብ ፊርማ ሲያሠባስብ የቆየው አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ህጉን ለማሠረዝ የሚያስችል በቂ ድምፅ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ከ1ሚ. በላይ ፊርማ አሰባስቤአለሁ ያለው ፓርቲው፤ የህዝቡን ፊርማ በመያዝ ክስ እንደሚመሰርት ገልጿል፡፡ ፓርቲው ለ3 ወራት ባካሄደው ፊርማ የማሰባሰብ ዘመቻ የፀረ ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ የሚያስችል ድምጽ ማግኘቱን የገለፁት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ፤ አሁንም ድረስ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኦንላይን እየፈረሙ በመሆኑ አጠቃላይ የፈራሚዎቹን ቁጥር መግለጽ ቢያዳግትም፣ እስካሁን ከ1 ሚሊዮን በላይ ፊርማ መሰባሰቡን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ የተሰባሰበው የፊርማ ብዛት ፓርቲው ከገመተው በላይ ስኬት መቀዳጀቱን ይጠቁማል ያሉት ሃላፊው፤ በአጠቃላይ የተሰበሰበውን የፊርማ ብዛት ፓርቲያቸው በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። “አንድነት” ፓርቲ በፀረ ሽብር ህጉ ላይ ያለው አቋም ሙሉ ለሙሉ ይሰረዝ የሚል እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ዳንኤል፤ የተሰበሰበውን የህዝብ ፊርማ ለፍ/ቤት በማቅረብ፣ ህጉ ከህገመንግስቱ ጋር እንደሚጋጭና የዜጐችን መሠረታዊ መብት እንደሚጥስ በመጥቀስ ክስ እንመሠርታለን ብለዋል። ከፍ/ቤት ቀጥሎም ጉዳዩን ለፌደሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ የገለፁት ሃላፊው፤ ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም በህዝብ ድምፅ ህግ የማሠረዝ እንቅስቃሴ ተሞክሮ ባያውቅም ፍ/ቤቶች እና ምክር ቤቱ የፓርቲውንና የፈራሚውን ህዝብ ጥያቄ ተቀብለው ውሳኔ እንደሚሰጡ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጐችን ድምፅ ዝም ብለን ሜዳ ላይ አንጥልም ያሉት አቶ ዳንኤል፤ የፍ/ቤቶች ገለልተኝነት አጠያያቂ ከመሆኑ አንፃር ጥያቄው ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን ህዝቡ የተሣተፈበት የፓርቲው የትግል አካል ተደርጐ ለታሪክ ተመዝግቦ ይቀመጣል ብለዋል፡፡ ህጉ ይሠረዝ የሚል አቋማቸው በመንግስት በኩል “ለሽብርተኝነት ድጋፍ ከመስጠት አይለይም” የሚል ትችት ማስከተሉን ያነሳንባቸው አቶ ዳንኤል በሰጡት ምላሽ፤ “የወንጀለኛ ህጉ አልበቃ ብሎ የፀረ-ሽብር ህግ ራሱን ችሎ የሚያስፈልግ ከሆነም ከውጭ የተቀዳ ሣይሆን ከፍተኛ የህግ ባለሙያዎች የተሣተፉበት እንዲሁም ህብረተሠቡ በየደረጃው ውይይት ያደረገበትና የመላውን ህዝብ ይሁንታ ያገኘ ህግ ማውጣት ይቻላል” ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አንፀባርቀዋል፡፡ ፓርቲያቸው በስራ ላይ ያለው የፀረ – ሽብር አዋጅ እንዲሠረዝ ጥብቅ አቋም የያዘበትን ምክንያት ሲያስረዱም፤ “ህጉ ከወጣ በኋላ በቀጥታ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ለማስፈራሪያና ለማጥቂያ በመዋሉ ነው” ብለዋል – ሃላፊው፡፡ የፀረ – ሽብር ህጉን ለማሠረዝ የሚያስችል ድምጽ ማሠባሠብ መቻላችን አገሪቱ አቤቱታ ለማቅረብ ምቹ የዲሞክራሲ ቁመና ላይ መገኘቷን ፈፅሞ አያመለክትም ያሉት አቶ ዳንኤል፤ ፓርቲያቸው የፀረ-ሽብር አዋጁን በተመለከተ ህጋዊ መነሻ ይዞ ለመላ ኢትዮጵያውያን በይፋ የተቃውሞ ጥሪ ያቀረበ ቢሆንም ሠሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየተላለፈ በሚገኘው ዘጋቢ ፊልም ላይ “አንድነት ፀረ-ሠላም ለማድረግ መሞከሩ ተገቢ አይደለም” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ በ97 ምርጫ ትልቁ የኢህአዴግ አጀንዳ “ኢንተርሃሞይ” እንደነበር ያስታወሱት ሃላፊው፤ በ2002 ምርጫ “ተቃዋሚዎች አጀንዳ የላቸውም” ወደሚል ቅስቀሣ መቀየሩን ጠቁመው፤ ለቀጣዩ ዓመት ምርጫ ደግሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን “ፀረ-ሠላም ናቸው” የማለት እንቅስቃሴ ከወዲሁ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል ፓርቲው፤ ከዚህ ቀደም ሠላማዊ ሠልፍ እንዳላደርግ እንቅፋት ሆነውብኛል ባላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ፖሊስ ላይ ክሡን ለመመስረት በዝግጅት ላይ እንደሆነ አቶ ዳንኤል ተናግረዋል፡፡ በዛሬው እለት አዲስ በተመረጡት የፓርቲው ሊቀመንበር በኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ይፋ የሚደረገው የፓርቲው ካቢኔ የመጀመሪያ ስራ፣ የፀረ – ሽብር አዋጁን ማሠረዝ እና ክስ የሚቀርብባቸው አካላት ላይ ክስ መመስረት እንደሚሆን ሃላፊው አክለው ገልፀዋል፡፡ - See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=6059#sthash.y3fRfyhQ.dpuf
Monday, December 30, 2013
በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ::
በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ::
ጅምላግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል!
ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙየቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡
...
በዚህ ሂደት ላይ ነውእንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህየተደናገጡት ሰራተኞችለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩዉስጥ ተገኙ፡፡
በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆንበአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እናበስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉምበወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነአስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ
ሙከራ ያደረጉት ሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰውአለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡ ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎችበመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችንስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆንየሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህne ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡምተደምጠዋል! በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!

Thursday, December 19, 2013
በጅጅጋ ከተማ ታቆሽሻላችሁ ተብለው ከታሰሩት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ
በጅጅጋ ከተማ ታቆሽሻላችሁ ተብለው ከታሰሩት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ
9ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በጅጅጋ ለማክበር ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ከተማ ያቆሽሻሉ ተብለው ተይዘው ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ ከምትገኘዋ ቀብሪበያህ እስር ቤት እንዲገቡ ከተደረጉት መካከል ከ40 በላይ ሰዎች ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በመሞታቸው በታሰሩበት አካባቢ እንዲቀበሩ ተደርጓል። ሟቾቹ በደንብ ባለመቀበራቸውና የአንዳንዶችን አስከሬን ጅብ አውጥቶ ስለበላው፣ ሌሎቹ ከእስር ቤቱ ራቅ ብለው በድጋሜ እንዲቀበሩ መደረጉን ኢሳት ከክልሉ ባለስልጣናት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በህይወት የተረፉት ሰዎች ከትናንት ጀምሮ የተለቀቁ ሲሆን፣ የዘመዶቻቸውን መሞት የተረዱ አንዳንድ ቤተሰቦች ሀዘን ተቀምጠዋል። ...
"ከተማ ታቆሽሻላችሁ እና ለጸጥታ ስጋት ትሆናላችሁ" በሚል ምክንያት ታስረው ከነበሩት ሰዎች መካከል ፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ በጋሪ መግፋት እና በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች፣ አይነ-ስውሮች፣ አካለ ስንኩላን፣ መታወቂያ አሳዩ ሲባሉ የክልሉን መታወቂያ ማሳየት ያልቻሉ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች በመምጣታቸው ጸጉረ ልውጥ ተብለው የተያዙ የሌላ አካባቢ ነዋሪዎች ይገኙበታል። በጅጅጋ መታወቂያ ለማውጣት 1 መቶ 15 ብር የሚጠይቅ ሲሆን፣ በችግር ምክንያት መታወቂያ ያላወጡና በድንገት መታወቂያ በተጠየቁበት ጊዜ ማሳየት ያልቻሉ በርካታ ሰዎች በእስር ቤት ውስጥ እንዲያሳልፉ ተደርገዋል።
የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ሃለፊ የሆኑትን አቶ አብዱላሂ ኢትዮጵያን ለማግኘት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልላቸውም ልናገኛቸው አልቻልንም።
በአገር ውስጥ ያሉ ወይም በውጭ የሚኖሩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ ጋዜጠኞች ወይም የቀይ መስቀል ሰራተኞች ሰዎቹ የተቀበሩበትን ቦታ ቦታው ድረስ ሄደው በማየት መረጃውን ይፋ እንዲያደርጉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች ጠይቀዋል። አካባቢው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በብዛት የሚንቀሳቀሱበት በመሆኑ ያለክልሉ ፈቃድ ፎቶግራፎችን ማንሳት አይቻልም።
መንግስት የብሄር ብሄረሰቦች በአሉ የለምንም የጸጥታ ችግር ማለፉን ቢገልጽም፣ በጸጥታ እና በገጽታ ግንባታ ስም ዜጎች ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ።
በጅጅጋ የተካሄደውን ዝግጅት በአብዛኛው ከህወሀት ጋር ዝምድና ያላቸው ሰዎች እንዳዘጋጁ ኢሳት መዘገቡ ይታወቃል። ከውስኪ አቅርቦት እስከ በዛር ዝግጅት፣ ከማስታወቂያ ስራ እስከ እቃ አቅርቦት በአብዛኛው የህወሀትና ከህወሀት ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች እንዳዘጋጁትና በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንዳገኙበት የደረሰን መረጃ ያመለክታል።See More

Monday, December 16, 2013
አንድ ወጣት የመንግስት ሰራተኛ መንግስትን በመቃወም ራሱን አጠፋ
አንድ ወጣት የመንግስት ሰራተኛ መንግስትን በመቃወም ራሱን አጠፋ
በሲዳማ ዞን በአለታ ጩኮ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤ ባለሙያ የሆነው ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ በሙያው ለአመታት ህብረተሰቡን ሲያገለግል ቢቆይም የመንግስትን አሰራር በተደጋጋሚ በመተቸቱ፣ ከመስርያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ግዜያት ግጭት ውስጥ ከመግባቱም በላይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሳይቀር ደርሶት ነበር።
ወጣት ነጋኝ ፀጋዬ መንግስትን በግልፅ በመቃወም፤ መስተካከል ያለበትን ጉዳይ በግልፅ መናገር ልዩ ባህሪው እንደነበር የሚናገሩት ጓደኞቹ፣ በዚህ ባህሪው በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጎም ነበር። "መቼ ነው ነፃ የምንወጣው?' በማለት በተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ እንደነበር የሚናገሩት ባልደረገቦቹ፣ ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓም አዋሳ አውሮፕላን ማረፍያ ሜዳ ላይ 20 ገፅ ያለው መንግስትን የሚቃወም ደ...ብዳቤ ፅፎ የትምህርት ዶክመንቶቹን እንደታቀፈ እራሱን አጥፍቶ ተገኝቷል።
በሰዓቱ ደርሰው ደብዳቤውን ያነበቡ ሰዎች እንደተናሩት ደብዳቤው
‹‹ እስከዛሬ ነፃ እወጣ ይሆን ብዬ ጠብቄ ነበር ግን ነፃ የምወጣበት መንገዱ እየጠበበ ነፃነቴ እየራቀኝ መጣ፣ ታዲያ ነፃ እንዲያወጣኝ በማን ተስፋ ላድርግ? 'በማንም … 'ለካ ነፃ መውጣት ይቻላል፣ እኔ ግን በቀላሉ እራሴን ነፃ ማውጣት እንደምችል ተረድቻው ፣ ስለዚህ እራሴን ከመራር ግፍ አላቅቄ በነፃነት ነፃነቴን አውጃለሁ፤ ስለዚህም ሞቴ ነፃነቴ ነው፡፡ ሳልገድል ፣ በሞቴ እራሴን ነፃ አወጣለው ››.. የሚል ይዘት አለው።
በግል ማስታወሻው ላይ ደግሞ ‹‹ በዚህች ሀገር ላይ ሶስተኛ አራተኛ አምስተኛ ዜጋ ሆኜ መኖሬ የሚያበቃው መቼ ነው ›› ኢትዮጵያ ነፃ መውጣት ባትችል እኔ ግን እራሴን በሞቴ ነፃ አወጣለሁ የሚል መልዕት" ሰፍሯል።
ወጣት ነጋልኝ ፀጋዬ የፃፈው 20 ገፅ የተቃውሞ ደብዳቤ በአሁን ሰዓት በአዋሳ ፖሊስ እጅ የሚገኝ ሲሆን ለቤተሰብ እና ለጓደኞቹ ደብዳቤውን ለመስጠት ፖሊስ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ወጣቱ በ30 ዓመቱ ይህችን አለም የተሰናበተ ሲሆን ስርዓተ ቀብሩ በጌደኦ ዞን ዲላ ከተማ ዲላ ኢየሱስ ቤ/ክ ታህሳስ 5 ቀን 2006 ዓ.ም ተፈፅሟል፡፡
ወጣት ነጋልኝ በጉራጌ ዞን ልዩ ስሙ ሜልኮ ተብሎ ከሚጠራው መንደር በ1976 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን ትምህርቱን በዲላ ከተማ እና በሀዋሳ ከተማ የተማረ መሆኑንም ከቤተሰቦቹ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ወጣቱ በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ1998ዓ.ም በማዕረግ ተመራቂ ስለመሆኑም የኮሌጁ ቆይታው ያሳያል።
ወጣት ነጋልኝ በሲዳማ ዞን በሎካ አባያ ወረዳ ለሁለት ዓመታት ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም ሲሰራ ከቆዬ በኋላ ወደ አለታ ጩኮ ወረዳ የተዛወረ ሲሆን፣ ህይወቱ እስካለፈበት ዕለት ድረስ በስራ ላይ እንደነበረ ከስራው ጎን ለጎንም በ agricultural business management ከያርድስቲክ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የመጀመርያ ዲግሪውን ይዟል፡፡
ለሰዎች መብት ዘወትር የሚታገል በሃፊዎቹ ዘንዳ ጥያቄ በመጠየቅ እና ያላመነበትን ነገር በመከራከር ሃላፊዎቹን መልስ በማሳጣት የሚታወቅ እንደነበር የስራ ባልደረቦቹ ገልጸዋል።
ወጣት ነጋልኝ ፡ አልንና ዝም አልን በሚል ርእስ በጻፈው አጭር ግጥም እንዲህ ይላል
አልንና ዝም አልን
ሲሉ ሰማንና እኛም መልሰን አልን
ያሉትን አልንና መልሰን ዝም አልን
በዝምታ ውስጥ መልስ እንደላ ስላወቅን

Thursday, December 12, 2013
የማይከሰሱ ወንጀለኞች
በወያኔ የአገዛዝ ዘመን ሀገራቸን ላይ እየታየ ላለው የፓለቲካ አለመረጋጋትም ሆነ ከጊዜ ወደጊዜ አየተባባሰ የመጣው የኢኮኖሚ ድቀት መባባስ ከሚጠቀሱት ዋነኛ ምክንያቶች ወስጥ አንዱ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መሰፋፋት ነው ።
ሀገራቸን ላይ አየታየ ያለው የኑሮ ገጽታ ሰፊ ለዩነት መፈጠር ፤የፍት ህ መዛባት ፣ ወነጀል መስፋፋት ፣ዜጎች አንደሰው የመመኖር ህልውናቸው በአስከፊ ሁኔታ ማሽቆልቆል እና የመሳሰሉ ችግሮች መስፋፋት ዋነኛ ምክኒያት ነው ።
በሙስና የተጨማለቁ መሪዎች በዘረጉት ብልሹ ኣስተዳደር የህዝብ መገልገያ ሆኑ ተቋማተን ጨምሮ አያንዳንዱ ደርጀቶች ፣ ቢሮዎች ውስጥ ህጋዊ አገልገሎት ለማግኘት መስተናገድ የዜግነት መብት መሆኑ ቀርቶ ግዴታ አስኪመስል ጉቦ አንዲሰጡ በግልጽ ይጠይቃሉ ።
የፍትህ አካላት ከተራው ፓሊስ ጀምሮ አስከ ከፍተኛ ሀላፊዎች በር ለማለፍ ገንዘብ ከዜጎች መብት ይቀድሟል የባለጉዳዩ አጅ ካልተፈታ ጉዳዮን ለማስፈጸም ማሰብ ቀላል አይደለም ያለ አገባብ በመመላለስ የመጉላላት ቸግር ያጋጥማል
ፍርድ ቤት ለከሳሽም ሆነ ተከሳሽ ባለጉዳይ ከተጻፈው ህግ ይልቅ ባለጉዳዩ ባለው ስልጣን ወይም ግለሰቡ ባቀረቡት የጉቦ መጠን ይዳኛሉ ብዙ ወንጀለኞች ከፍርድ ነጽ የደረጋሉ ፣ በአንጻሩ ደሞ ንጹሃን ጉቦ ባለመስጠታቸው (አቅማቸው ባለመፍቀዱ) ፍት ህ ተጓድሎባቸዋል ፤ ዳኞች ፣ ኣቃቤህጎች አና ጠበቃዎች ጉቦ በመቀበል ፍርድ ያዛባሉ ።
የጤና ተቋማተም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ከሚፈጸምባቸው ቦታዎች ወስጥ ይጠቀሳሉ፤ ከክፍያ ነጻ የሆኑ መድሀኒቶች ለህሙማን በሽያጭ ይቀርባሉ ፤ የቅርብ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሀሙማን ለሰራተኞች የሚከፍሉት ጉቦ በማጣታቸው ብቻ በቂ ህክምና ባለማግኘታቸው ለሞት ያዳረጋሉ ።
በእምነት ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት ፣ በሰራተኛና ኣሰሪ ቅጥር ሂደት ፣ጉምሩክ ባለስልጣን መ`\ ቤት ፣ የጸረ ሙሰና መስሪያ ቤቱን ጨምሮ እያንዳንዱ የመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ በግልጽ እና በአስከፊ ሁኔታ ሙስና አየተስፋፋ ይገኛል ።
የመቅጫ ህጉ የማይመለከታቸው ይመስል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት (ህውሀት አባላት) ስልጣንን ያለ አገባብ በመተቀም የሀገሪቱን ገንዘብ ወደ ግል ካዝናቸው ሲያስገቡ ፣ የመንግስት ንብረት የሆኑ ትልልቅ ተቋማትን ወደግለሰብ ነብረትነት ሲያዞሩ፣ የውጭ ንግድ እና ምንዛሬው በጥቂት የህውሀት አባላት እጅ ቁጥጥር ውስጥ ሲወድቅ የሀገሪቱን መሬት ለጎረቤት ሀገር በመጽሸጥ የወንጀል ስራ ላይ ሲሰማሩ፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በጥቂት ባለስልጥናት እጅ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ሳለ (በ2013 በወጣው መረጃ መሰረት ሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ባለሀብቶች የመጀመሪያውን 10 ደረጃ የያዙት የህውሀት አባላት አና ከፍተኛ ባለስልጣናት መሆናቸው ይታወቃል ) ፤ የህ የሙስና መረብ ሁሉንም ባለስልጣናት ያስተሳሰረ በመሁኑ የክስ ሂደቱ ተገባራዊ እንዳይሆን ብሎም ሀገሪቱም ከገባችበት ዘቅት አንዳትወጣ እንቅፋት ሆኖኣል።
በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል ተብለው የቀረቡት የህውሀት አባል ባለስልጣናት ጉዳይ (ሌባ ሲሰርቅ ተስማምቶ ሲካፈል ይጣላል ) እንዲሉ የስልጣን ክፍፍል በፈጠረው ችግር ጠልፎ መጣያ የባለስልጣናቱ የግል ጸብ እንጂ ህግን ለማስፈጸም የተደረገ ሂደት አይደለም ፤ እውነት ሙስናን ለመዋጋት ቅርንጫፎቹን ሳይሆን ግንዱ የሆነውን (የህውሀት ባለስልጣናትን አና ስር አቱን ) ማስወገድ ብቻ ነው መፍሄው ።
Wednesday, December 11, 2013
በዋልድባ ላይ ለሚሰራው የሥኳር ፕሮጀክት ነዋሪዎች መነሳት ጀመሩ
#በዋልድባ
ላይ ለሚሰራው የሥኳር ፕሮጀክት ነዋሪዎች መነሳት ጀመሩ #የቆራሪት_ከተማ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በዋልድባ ገዳም ላይ ለሚገነባው የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመጀመሪያ ዙር
1800 አባወራዎች ከቦታቸው መነሳታቸው ታወቀ። ለተነሱ አር...ሶ አደሮቹ
127.5 ሚሊዮን ብር የካሳ ክፍያ ተሰጥቷል። ለእነዚህ ተነሺዎች ከወራት በፊት የገጠር ከተማ መልክ በመያዝ በተገነባችው የቆራሪት ከተማ ላይ የማስፈር ስራ ተከናውኗል። ለዚች ከተማ ምስረታ ምክንያት ደግሞ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚሰራው የስኳር ልማት ፕሮጀክት መሆኑ ታውቋል። በአሁኑ ሰዓት ከቦታው የተነሱት 1800 ነዋሪዎች ከወልቃይት ወረዳ ፤ ከቃሌማ እና ፅምሪ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው። መንግሥት እንደሚለው ለእነዚህ የልማት ተነሺዎች ለተነሱበት ቦታ በምትኩ የእርሻ ፤ የመኖሪያ ቤት ፤ ሙሉ የቤት እና የሰብል ካሳ ክፍያ ፈጽሜያለሁ ብሏል። ለአርሶ አደሮቹ ነዋሪዎች መንግሥት
127.5 ሚሊየን ብር ካሳ መስጠቱ ታውቋል ፤ በሁለተኛ ዙር የሰፈራ ፕሮግራሙ ላይ 4ሺህ ሰዎች ከቦታው ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሰፈራው የሚቀጥል ሲሆን ለሚነሱት ከ13 ለማያንሱ አብያተ ክርስቲያናት ምትክ አዳዲስ ቤተክርስቲያን በቆራሪት ከተማ መሰራት መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል። የዚህ ፕሮጀክት እሳቤ መነሻው 1991
ዓ.ም ቢሆንም አሁን ላይ ግን ወደ እውነታው እየተቃረበ ያለ ይመስላል ፤ ከዓመት በፊት ብዙ ሲያነጋግር የነበረው ይህ የሥኳር ፕሮጀክት አሁን ላይ የቁርጥ ቀኑ የቀረበ መስሏል ፤ መንግሥት ገዳሙን አልነካሁም በማለት አይኔን ግንባር ያድርገው እያለ ቢምልም መሀላው እውነታው ሊደብቀው አልቻለም። ገዳማውያኑም የሚደርስባቸው መከራ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱ ከቦታው የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ ጥቂት የማይባሉት መከራውን በመቋቋም የሚመጣውን ነገር ሁሉ በጸጋ ለመቀበል በአቋማቸው ፀንተው አሁንም ድረስ ያሉ ሲሆን ፤ ጥቂት መነኮሳት ግን የመንግሥትን የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከግብ ለማድረስ ቀን ከሌት ከመንግሥት ሹማምንት ጋር ዳገት ሲወጡ ቁልቁለት ሲወርዱ ተስተውሏል። የ2005 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥኳር ኮርፖሬሽን ዓመታዊ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበበት ጊዜ መንግሥት በበጀት እጥረት የሰፈራ ፕሮግራሙን በአግባቡ ለማስኬድ እንቅፋት እንደሆነበት ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ ማቅረባቸው ይታወሳል ፤ ከዚህ በተጨማሪም ቦታው ድረስ በመሄድ ስራውን የሚያከናውን የተማረ የሰው ኃይል እጥረት እና ቦታው ላይ ረዥም ጊዜ አለመቆየት መቻልን ለፕሮጀክቱ መጓተት እንደ ሁለተኛ ምክንያት አቅርበው ነበር። አንድ አድርገን ከውስጥ ሰዎች ባገኝችው መረጃ መሰረት በአሁኑ ሰዓት ዋልድባ ላይ እየተሰራ ላለው የሥኳር ፕሮጀክት የወራት ዝምታ መንስኤው ባለሙያዎች ቦታው ላይ ይህን ሥራ ለመስራት ፍቃደኛ አለመሆናቸው መሆኑን ለማወቅ ችላለች። በተለያዩ ጊዜም ለሥራ ወደ ቦታው ያቀኑ ባለሙያዎች በራሳቸው ፍቃድ ስራውን ያለደመወዝ እየለቀቁ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እኛስ የኃያሉን የአምላክን እጅ እጠብቃለን ።
Subscribe to:
Comments (Atom)