ጉድ በል ...ኣለ ኣሉ ፤ ገና ብዙ እንሰማለን። (ከታዘብኩት)
እንዲያው በዛው ሌላውንም ስምምነት በተመለከተ ጠቆም አርጎን ቢያልፍ ጥሩ ነበር አንጂ አለበለዛማ ወያኔ ያሳደደውን መጣሁልህ ሲባል አበባ ይዞ ዌል ካም ሲል ኣይተንም ሰምተንም ኣናውቅ።
ወይ ከዜሮ ዜሮ አቤት የቅንድቡ ማማር ካላለ፤ አለበለዛ አንደ ፱፯ቱ ምርጫ በሙስና ካልትጭበረበረ፥ ወይንም ደግሞ "አንደር ከቨር ሚሽን አኮምፕሊሽድ" ካላለን እኮ እንዴት ተደርጎ? እንዴት እንቀበል?
መለካት ያለብኝ በምሰራው ስራ መሆን ነው ያለበት የሚለን ጋዜጠኛ ዳዊት ደጋግሞ የሚናገራቸው በእስር ላይ ያሉ የሙያ ኣጋሮቹ ከእስር ሳይፈቱ ፤ እሱ እንዴት ወደ እስር ማገዶው ሔጀ በሰላም እሰራለሁ ብሎ ደፈረ? ምንስ ማረጋገጫ ቢኖረው ነው። CPJ (Committee to Protect Journalists) የሚባለዉ ስለ ነጻ ሚዲያ እና ስለ ጋዜጠኞች መብት ተሙዋጋች ድርጂት በሰፊዉ እንደሚዘግበዉ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኛ ሆኖ መገኘት እንደ ወንጀል በሚቆጠርበት ወቅት አና አስር አና አፈና የተባባሰ በሆነብት ጊዜ ላይ የመጉዋዝ ሞራሉስ ከየት መጣ? ይህ እንግዲህ ቀስ እያለ የሚገለጥ እውነታ ነው።
እስኪ ያረገውን ቃለ ምልልስ አንስማ ...