Bloomberg የተባለ የዜና ድህረ ገጽ እንደዘገበው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ 2012 አመተ ምህረት 160,000 የሚሆኑ ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ የባርነት ንግድ ወይም የጉልበት ስራ ወደ ሳውዲ አረቢያ ተጉዘዋል ፤በቅርቡ አየሰማናቸው ካሉት የሴት እህቶቻችን የስቅላት አና የሞት አንዲሁም የስቃይ ዜናዋች ከነዚሁ ውስጥ ይገኙበታል ማለት ነው።
Gulf Arab states በሚባሉት የአረብ ሀገራት Kuwait, Bahrain, saudi Arabia, United Arab Emirates በመሳሰሉት ሀገሮች ከኢትዮጲያ ወደነዚህ ሀገራት በቀን 1500 የሚሆኑ ወገኖቻችን ለጉልበት ስራ እንደሚሰደዱ UPPSALA UNIVERSITY June 2013 ለጥናት ምርምር ባቀረበው ጽሁፉ ላይ ገልጾል።
አጂጉን የሚያሳዝነው ነገር እነዚሁ ወገኖቻችን አገር ወገን ተቆርቆሪ እንደሌለው ባሰሪዋቻቸው ስቃይ እና በደል፤ መደፈር፤ ግርፋት፥ አንዲሁም ሰቀላ እንኩዋን ሲደርስባቸው በዛው አገር የሚገኘው የይስሙላ ኢትዮጲያ ኤምባሲ ኡኡ የድረሱልን ጥሪ እንኩዋን ሲባሉ ወግ ሆኖ እንኵዋ የዜጎችን መብት ሊያስከብር አና በህግ ሊጠይቅ ቀርቶ ባልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ቆሞ አስጨፍጫፊ ሆኑዋል።
ህግ አርቃቂ እና አውጭ ነገር ግን መተግበር አላርጂኩ የሆነው ዬኢትዮጲያ መንግስት በመተዳደሪያ ህገመንግስቱ ላይ ህገወጥ የሰው ንግድ ዝውውርን ሲፍጽም የተገኘ ከአምስት እስከ ሃያ አመት የእስር ቅጣት እንደሚያገኘው የደነገገ ሲሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግን መንግስት የዚሁ ህገወጥ የሰው ዝውውር ንግድ እረጂና ፈጽሚ ነው። ለምን ሲባል ለውጭ ምንዛሬ !
አፍንጫው ስር ሆነው የህጻናት፥የሴት አና የወንድሞቻችን ሀገወጥ የሰው ንግድ ዝውውር ገበያ የሚገበያዩትን ኤጀንሲዋች አላየሁም ቢል መሳቂያ ከመሆን አልፎ ,በጎንም እነዚሁን ዔጀንሲዋች እንደሚረዳ ግልጽ ነው። የወገኖቻችን ስቃይ አና ሞታቸው አፍጥጦ እንዲህ የሚዲያዎች ሁሉ መወያያ ሲሆን ግን ያው የተለመደ ፕሮፓጋንዳ ግድ ነው። አስቁመናል፤ አስረናል፤ ቀጥተናል ወዘተ፤ የስደቱስ ምንጬ ማቆሚያው ምንድን ነው? ወገኖቻችን ያለውን ስቃይ አና በደል እየሰሙ ፤እያዩስ አገራችው መኖር ከዛው ስቃይ ያለተናነሰ መሆኑን አይተው መርጠው የወጡት ለምንድነው? በባህር ፤ በበረሃ እንደዘበት በሞት እየቀሩ ፤ከተወለዱበት አገር ከተከፈሉበት ዘመድ እና ወገን አልባ ሆነው የቀሩት ለምን የሆን? እንግዲህ አለም ይቁጠረው!
ሌላው በጣም የሚያሳዝነው እና ልብ የሚሰብረው ጉዳይ የሴት እህቶቻችን ስቃይ እና ጥቃት በባእዳን አገር አና ወገን ብቻ ሳይሆን ባገራቸው ላይ በገዥው መንግስት ባለስልጣናት እና ታጣቂ ወታደሮችም መሆኑም ጭምር ነው። allAfrica የተባለ የዜና ደህረ ገጽ እንደዘገበው በ 2011 February በኦጋዴን የሚገኙ የኢትዮጲያ ሶማሌ ሴት እህቶቻችንን የኦጋዴን ነጻ አውጭ(ONLF) ደግፋችዋል በማለት በዔሌክትሪክ ሾክ በማሰቃየት፤ በእሳት በመጥበስ አንዲሁም በእስር ስቃይ የተፈጸመባችውን የሴት እህቶቻችንን ስቃይ ከፎቶ ማስረጃ ጋር በተደገፈ አቅርቦል።
መቸስ ሌላው ሌላውን በደል እና ስቃይ እንዲሁም የመንግስት አፈና ቤት ይቁጠረው ብለን ነው። ያዲስ አበባ እስር ቤቶች ፤ማእከላዊ እና ቃሊቲ፤ አንዲሁም ሌሎች የየክፍለሃገር እስር ቤቶች ያጎሩትን ፤ ቤት ይቁጠረው ነው።
http://allafrica.com/view/photoessay/user/user/id/201102100001.html
http://www.youtube.com/watch?v=ZvuErWmFw3I

