Friday, October 25, 2013

በእስር ላይ ያሉ የሙያ ኣጋሮቹ ሳይፈቱ እሱ እንዴት ወደ እስር ማገዶው ደፈረ?


ጉድ በል ...ኣለ ኣሉ ፤ ገና ብዙ እንሰማለን። (ከታዘብኩት)

እስኪ ይታያችሁ በአሁን ሰኣት እየተባባሰ  በመጣው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የሰባዊ መብት እረገጣ፤ እስራት እና የነጻ ሚዲያ አፈና ፤ እስር ቤት ውስጥ ታጉረው ያለፍትሕ በሃሰት ክስ ተመስርቶባቸው በስቃይ ላይ የሚገኙ ብዙሃን ጋዜጠኞች ባሉባት ኢትዮጲያ ፤ያውራምባ ታይምስ ድህረ ገጽ ዋና አዘጋጂ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሁለት አመት በፊት መንግስት በሚፍጽመው ህገወጥ ተግባር እና ኢ ሰብአዊ ድርጊት ነቅፌና ተቃውሜ በመጻፌ በመንግስት እንደ ህገ ወጥ በመቆጠሬ፤በመወንጀሌ እና ለእስር በመፈለጌ ከሃገሬ ተሰደድኩ የሚለው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ኣሁን ደሞ ከሁለት አመት በሁዋላ ሊያስረው ይፈልገው ወደነበረው መንግስት በራሱ ኣንደበት፤ባደባባይ ልመለስ ነው ይለናል። ለምን ሲባል ስራየን በጥራት እና በብቃት ለመስራት አዛው ቦታው ምንጩጋ መሆን እንዳለበት ኣሁን ስለተገለጠልኝ ነው ይለናል። 
እንዲያው በዛው ሌላውንም ስምምነት በተመለከተ ጠቆም አርጎን ቢያልፍ ጥሩ ነበር አንጂ አለበለዛማ ወያኔ ያሳደደውን መጣሁልህ ሲባል አበባ ይዞ ዌል ካም ሲል ኣይተንም ሰምተንም ኣናውቅ።
ወይ ከዜሮ ዜሮ አቤት የቅንድቡ ማማር ካላለ፤ አለበለዛ አንደ ፱፯ቱ ምርጫ በሙስና ካልትጭበረበረ፥ ወይንም ደግሞ "አንደር ከቨር ሚሽን አኮምፕሊሽድ"  ካላለን እኮ እንዴት ተደርጎ?  እንዴት እንቀበል?  

መለካት ያለብኝ በምሰራው ስራ መሆን ነው ያለበት የሚለን ጋዜጠኛ ዳዊት ደጋግሞ የሚናገራቸው  በእስር ላይ ያሉ የሙያ ኣጋሮቹ ከእስር ሳይፈቱ ፤ እሱ እንዴት ወደ እስር ማገዶው ሔጀ በሰላም እሰራለሁ ብሎ ደፈረ? ምንስ ማረጋገጫ ቢኖረው ነው።  CPJ (Committee to Protect  Journalists) የሚባለዉ ስለ ነጻ ሚዲያ እና ስለ ጋዜጠኞች መብት ተሙዋጋች ድርጂት በሰፊዉ እንደሚዘግበዉ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኛ ሆኖ መገኘት እንደ ወንጀል በሚቆጠርበት ወቅት አና አስር አና አፈና የተባባሰ በሆነብት ጊዜ ላይ የመጉዋዝ ሞራሉስ ከየት መጣ? ይህ እንግዲህ ቀስ እያለ የሚገለጥ እውነታ ነው።  

እስኪ ያረገውን ቃለ ምልልስ አንስማ ...




Is his mission accomplished ?

Awramba Times Editor is going back home
 
 

Tuesday, October 22, 2013

"በአዲስ አበባው ፍንዳታ የሞቱት ኢትዮጵያዊያን ናቸው"

“አትፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም” ዶ/ር መረራ
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ሰፈር የደረሰውን ፍንዳታ አስመልክቶ ኢህአዴግ ያሰራጨውን ዜና የሚቃረኑ መረጃዎችና አስተያየቶች ቀረቡ። ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የድጋፍ አስተያየት ሲሰጡ ዶ/ር መረራ “አትፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ አያጠፋም” ሲሉ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በፍንዳታው የሞቱት ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲል ስም ገልጾ የኢህአዴግን ዜና አጠጥሎታል።
በፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቁት ከኢህአዴግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚታሙ ፓርቲዎች “የጸረ ሽብርተኞች አዋጅ ሊጠናከርና ሊጠብቅ ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የኢራፓ፣ የኢሴዳፓ፣ ቅንጅትና አዲአን ተወካዮች በየተራ የኢህአዴግን ዜና የሚቃወሙና በጥርጣሬ የሚመለከቱትን አውግዘዋል። በወቅቱ የቴሌቪዥን ጣቢያውም አንድነትና የሰማያዊ ፓርቲ ጠርተውት በነበረው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ “የጸረ ሽብርተኛነት አዋጅ ለሌላ ተግባር መዋሉን እንቃወማለን” በማለት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ በማሳየት ዜናውን ለማጀቢያነት ተጠቅሞበት ነበር።
በግል አስተያየታቸውን የተጠየቁት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው “ብዙዎች፣ እኔም ጓደኞቼም በጥርጣሬ ነው ያየነው” ሲሉ ከተቆረጠው ንግግራቸው ተደምጧል። ዶ/ር መረራ “አጥፍቶ ጠፊ አጥፍቶ ይጠፋል እንጂ በሜዳ ዝም ብሎ ራሱን አያጠፋም” ካሉ በኋላ “ስለዚህ እውነት ተደርጓል?” የሚለው ትልቁ ችግርና የጥርጣሬው መነሻ እንደሆነ አመልክተዋል።
ስለዚህ በሚል ድምዳሜ “ሰው አንዳንድ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ለራሱ ፖለቲካ ብሎ የሚያደርገው ያው የለመደው ስራ ነው” እንደሚል ዶ/ር መረራ በተቀነጨበው አስተያየታቸው ሲናገሩ ተሰምቷል። በተቃራኒ ከላይ በስም የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማና የአልሸባብ ስጋት ላይ ያለች አገር በመሆኗ ኢህአዴግ ህዝብን የመጠበቅና ደህንነትን የማስጠበቅ አደራ ስላለበት እነሱን ጨምሮ እንዲጠብቃቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስሙ የሚነሳውና በታጣቂ ሃይሉ ፈርጣማነት የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ  /ትህዴን/ በቦሌ ክፍለ ከተማ በቤት ውስጥ ፈነዳ በተባለው ፈንጂ ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለጸው ሁለት የሶማሌ ዜጎች አይደሉም ሲል ከሁሉም ወገን የተሰራጨውን ዜና በዜሮ አጣፍቶታ። በፈንጂው የሞቱት ሁለት ሰዎች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ስማቸውም “ምክትል ኢንስፔክተር ሞላ መላኩ የተባሉ የፖሊስ አባልና አቶ ሞገስ አስቻለው የተባሉ ሲቪል ናቸው” ሲል የገለጸው ትህዴን የሟቾቹ ስም በመታወቂያ መረጋገጡን አመልክቷል።የመታወቂያውን ቅጂ ግን በገጹ አላተመም። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በስፍራው ታይታችኋል በሚል በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን በመግለጽ የሶስት እስረኞችን ስም ይፋ ያደረገው ኦክቶበር 19 ቀን 2013 በራሱ ኦፊሳላዊ ድረገጽ ላይ ነው። ኢህአዴግም ቢሆን ሞቱ የተባሉትን ሰዎች ይህ ዜና እስከተጻፈበት ቀን ድረስ በሰነድ አስደግፎ አላቀረባቸውም።
በሌላ በኩል ኦክቶበር16 ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት 3ቀን 2006ዓ.ም. በቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ማዞሪያና ቦሌ ሚካኤል መግቢያ አካባቢ በቦምብ ፍንዳታ ሕይወታቸው ያለፈው ሁለት ሶማሊያውያን ሽብርተኞች መሆናቸውን ማረጋገጡን፣ የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ማስታወቁን ዘግቧል።
Bomb-Blast-Addisየአንድ ግለሰብ ሰርቪስ ቤት ተከራይተው ከነበሩት ሶማሊያውያኑ መካከል፣ አንደኛው ከ20ቀናት በላይ የቆየ ሲሆን፣ ሌላኛው ፍንዳታው ከመድረሱ ከሁለት ሰዓታት በፊት የደረሰ መሆኑን ግብረ ኃይሉ ማረጋገጡን ያመለከተው ሪፖርተር ሽብርተኛ የተባሉት ሶማሊያውያኑ ካፈነዱት ቦምብ በተጨማሪ መጠናቸው ያልተገለጸ ቦምቦችና አንድ ሽጉጥ ከሁለት ካርታ ጥይት ጋር መገኘቱን፣ የፈንጂ ማቀጣጠያና የአደጋ መከላከያ ጃኬቶች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሊያና ቀበቶዎች መገኘታቸውም ጠቁሟል፡፡ ከሶማሊያውያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎችና የቤቱ አከራይ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄባቸው መሆኑንም ግብረ ኃይሉ አክሏል በማለት ሪፖርተር ዘግቧል። አዲስ አድማስ በበኩሉ አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነት መውሰዱን አድራሻው አልተመዘገበ የትዊተር ማረጋገጫ በማመላከት ከዚህ በታች ያለውን ዜና አስነብቧል።
ባለፈው እሁድ በቦሌ ሚካኤል አካባቢ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ሁለት ተጨማሪ የፍንዳታ ጥቃት ለማድረስ አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ቡድን እንደዛተ የገለፀው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ የዛቻው ተአማኒነት ባይረጋገጥም በኢትዮጵያ የሚገኙ አሜሪካዊያን ጥንቃቄ እንዳይለያቸው ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ በመግለጽ ዜናውን የከፈተው አዲስ አድማስ፣ “የኢትዮጵያና የናይጄሪያ ቡድኖች ግጥሚያ በሚካሄድበት ሰዓት ጥቃት ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ሁለት ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በማወጅና ሽብር ለመፈፀም በመዛት የሚታወቀው አልሸባብ “ድርጊቱ በኔ አባላት የተፈፀመ ነው” ብሏል በማለት አልሸባብ በቦሌ ሚካኤል ለተከሰተው ፍንዳታ ሃላፊነት እንደሚወስድ በትዊተር እንዳስታወቀ ማሰራጨቱን፤ በፒያሳና በቸርችል ጐዳና አካባቢ የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እንደዛተም ገልጿል፡፡
በቦሌ ሚካኤል በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተከሰተው ፍንዳታ ሁለት የሶማሊያ ተወላጆች መሞታቸውን የገለፀው ፖሊስ፤ ከሟቾቹ አንዱ የኢትዮጵያ ማሊያ በመልበስ ከኳስ ተመልካቾች መሃል የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ እንደነበር መጠቆሙን አዲስ አድማስ በዜናው አውጇል። አዲስ አድማስም ሆኑ ሪፖርተር ፖሊስ የነገራቸውን ከመዘገብ ውጪ ከሌሎች ሚዲያዎች፣ በተለያዩ ማህበረ ገጾችና በቅርበት ከህብረተሰቡ የሚሰጡትን አስተያየቶች አስመለክቶ ዜናውን ላቀበላቸው ክፍል አላቀረቡም።
የኢህአዴግ አንደበትና የንግድ ድርጅት የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የደረሰው የፈንጂ ፍንዳታ በሁለት ሶማሊያውያን አሸባሪዎች የተፈፀመ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል አሰፋ አብዩን ጠቅሶ አስታውቋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳለው ፍንዳታው የደረሰው በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ቀበሌ 01 በተለምዶ ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በአንድ የመኖሪያ ቤት ውስጥ ነው። ፖሊስ ፍንዳታው ፈንጂ መሆኑንና በጥቅም ላይ የዋለው ቲ ኤም ቲ የተባለ የፈንጂ ዓይነት መሆኑን እንደደረሰበት አረጋግጧል። ፍንዳታውንም ሁለት ሶማሊያውያን ማቀነባበራቸውን ፖሊስ እንዳረጋገጠና ግለሰቦቹ የአሸባሪ ቡድኑ አልሸባብ አባል መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን ጄኔራል አሰፋ አብዩ መናገራቸውን የጠቆመው ፋና ከሁለቱ አሸባሪዎች መካከል አንደኛው ወገቡ ላይ የታጠቀና ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር የተዘጋጀ መሆኑን ያመላክታል ብሏል።
ሌላኛው አሸባሪ በሻንጣ ፈንጂ የያዘ ሲሆን፥ የፈነዳውም ፈንጂ በሻንጣው ውስጥ የነበረ መሆኑን ነው ጀነራል አሰፋ ያስረዱት። ለአጥፍቶ ጠፊ ተግባር ሲዘጋጅ የነበረው ግለሰብ የታጠቀው ፈንጂ ግን እንዳልፈነዳ አመልክተዋል። አሸባሪዎቹ በአጠቃላይ ሶስት ፈንጂዎችንም ይዘው ነበር። አሸባሪዎቹ ህዝብ ባለበት ስፍራ አደጋ ለማድረስ ተከራይተው በነበሩበት ቤት ውስጥ ሲዘጋጁ ፍንዳታው ደርሷል ብሎ ፖሊስ እንደሚጠረጥር ነው የጠቆሙት። ከአሸባሪዎቹ ጋር ፖሊስ የእጅ ቦምቦችንና ሽጉጥ ከነጥይቱ አግኝቷል።
የፋናን ዜና ተንተርሶ የተሰነዘሩ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ሪፖርተር በፈነዳው ፈንጂ ህይወቱ ያለፈው አንደኛው ሰው ሰውነቱ መበታተኑና የአይን እማኞችን ገልጾ መዘገቡን ያስታውሳሉሉ። ፈነዳ የተባለው ፈንጂ ከፈነዳ በሁዋላ አጥፍቶ ለመጥፋት የተዘጋጀው ሰው የታጠቀው ፈንጂ አለመፈንዳቱ መገለጹ ከሙያ አንጻር ጥያቄ የሚያስነሳ እንደሆነ፣ ከዚህም በላይ ድርጊቱን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ጋር ለማገናኘት የብሔራዊ ቡድን መለያ ሹራብ ተገኘ መባሉ ድርጊቱን ድራማ ያስመስለዋል ባይ ናቸው። (ፎቶ: ሪፖርተር)

Saturday, October 12, 2013

የሕዳሴ ግድብ ቦንድ እንድንገዛ እየተገደድን ነው


ሞትን ተጋፍጠው  የተለያዩ አሰቃቂ ግፍ እና መከራን ታግሰው የድሀ ቤተሰባቸውን ያእለት ጉርስ ፍለጋ በጨቅላ እድሜአቸው ወደ አረብ ሀገራት ስደት የተዳረጉ ወገኖቻችን ከሞት ጋር ተናንቀው የሚቐጥሩትን ጥሪት በግድ ማሰፈታት ገግፍም በላይ ነው ፡፡
በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች እና በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የኤምባሲና የቆንፅላ ፅ/ቤት አገልግሎቶችን ለማግኘት የሕዳሴ ግድብ ቦንድ እንድንገዛ እየተገደድን ነው አሉ፡፡ “ሁሉም ስደተኛ ተሰብስቦ ያሳለፈው ውሳኔ ስለሆነ የግድ ቦንድ መግዛት አለባችሁ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ስደተኞቹ ተናግረዋል፡፡ በአባይ ወንዝ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተስማማበት ፕሮጀክት እንደመሆኑ፣ እኛም ድጋፋችንን በተለያየ መንገድ በመስጠት ላይ ነን የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ የገንዘብ መዋጮውና የቦንድ ግዢው የግዴታ መሆኑን ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
የቦንድ ግዢም ሆነ መዋጮ በዜጎች ፈቃደኝነት የሚፈፀም እንደሆነ መንግስት በተደጋጋሚ እየገለፀ መመሪያ ሲያስተላልፍ እንደነበር ያስታወሡት ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ይሁን እንጂ በዱባይ እና በሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲዎች ወይም የቆንፅላ ፅ/ቤቶች ግን ፓስፖርት ለማሣደስና ሌሎች አገልግሎቶች ለማግኘት ስንሄድ፣ ቦንድ እንድንገዛ እንገደዳለን ብለዋል፡፡ ለ10 አመታት ከሚኖርበት ከሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ሣምንት ለእረፍት ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን የሚናገረው ጀማል አረቦ ኢስማኤል፤ ቢያንስ በ500 ሪያል (ወደ 3ሺ ብር ገደማ) ቦንድ መግዛት አለብህ እንደተባለ ገልጿል፡፡ ቅሬታቸውን ለኤምባሲዎችና ለቆንስላ ፅ/ቤቶቹ አቅርበው እንደሆነ ተጠይቆ ጀማል ሲመልስ፤ ብዙ ስደተኞች በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውን ጠቅሶ፣ መፍትሄ ግን አልተሰጠንም ብሏል፡፡
“ቃል ስለገባችሁ በቃላችሁ መሠረት የቦንድ ግዢውን ፈፅሙ” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው አቶ ጀማል ገልጿል፡፡ የቦንድ ግዢ በእያንዳንዱ ሰው ፈቃደኝነትና ውሳኔ እንጂ፣ የተወሰኑ ሰዎች ተሰብስበው ወስነዋል ተብሎ በሁሉም ሰው ላይ ግዴት የሚጫን መሆን የለበትም ብሏል - ጀማል፡፡ “ስንቸገር ዞር ብሎ ያላየንና በችግራችን ጊዜ ያልደረሠልን ኤምባሲ፤ የዜጐችን የላብ ውጤት በአስገዳጅ ሁኔታ መቀማቱ ተገቢ አይደለም” የሚለው ጀማል፤ ሁሉም ነገር በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ይላል፡፡ በሳዑዲ አረቢያ ለ6 አመት የኖረው ሌላው ወጣት በበኩሉ፣ በርካቶች ለቦንድ ግዢ የሚጠየቁትን ክፍያ በመሸሽ ወደ ኤምባሲው አገልግሎት ለማግኘት መሄድ እንደማይፈልጉ ተናግሯል፡፡
“እያንዳንዱ ዜጋ ቦንድ ግዢውን በፍቃደኝነት ብቻ ነው የሚሣተፈው፤ በምንም ሁኔታ አይገደድም” የሚለውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ቃል አስታውሶ፣ አሁን ግን ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም ብሏል፡፡ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ በዱባይ የምትኖር ሌላዋ አንዲት ወጣት፤ ፓስፖርት ለማሣደስ ወደ ቆንፃላ ፅ/ቤቱ ብታመራም 1000 ድርሃም ካልከፈልሽ አገልግሎት ማግኘት አትችይም መባሏን ገልፃለች። 500 ድርሃም ለቦንድ ግዢ ሲከፈል ቀሪው 500 ደግሞ ይህን ጉዳይ ለማስፈፀም ለተቋቋመው ኮሚቴ ተብሎ ይከፈላል የምትለው ኢትዮጵያዊቷ፤ ክፍያው ካልተፈፀመ ከማንኛውም የቆንስላ ፅ/ቤት አገልግሎት ማግኘት አይቻልም ብላለች፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ በስልክ አግኝተን ያነጋገርናቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ “ይሄ ስለመፈፀሙ የተጨበጠ መረጃ የለንም፣ ነገር ግን ማስገደድ ተቀባይነት የሌለውና ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡ ተገቢ እንዳልሆነ ከዚህ በፊትም ተነግሯል” ብለዋል፡፡ አክለውም “ይሄ ድርጊት ተፈፀመብን የሚሉም ጥቆማውን ለመስሪያ ቤታችን ማሣወቅ ይችላሉ” ብለዋል፡፡
 AddisAdmassNews.com

Thursday, October 10, 2013

ድሆችን ያፈናቀለው “ኢንቨስትመንት” ዕዳ ዋጠው

anuak man“መሬታችንን ለምን እንነጠቃለን?” በማለት የጠየቁ ተገድለዋል። ተገርፈዋል። ታስረዋል። አሁን ድረስ እስር ላይ የሚገኙ አሉ። ባዕድ እንኳን ባልሞከረው የከፋ ጭካኔ በከባድ መሳሪያ በተደገፈ የጦር ሃይል የተወለዱበትን መሬት እንዲለቁ የተገደዱ አዛውንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ እስከ ወዲያኛው የሚያሽር አይደለም። በሌሊት እርቃናቸውን ከሚያርፉበት ታዛ ስር ነፍጠኛ ሰራዊት እንዲከባቸው እየተደረገ የተፈጸመው አስነዋሪ ግፍ ጊዜ የሚጠብቅ እንደሆነ በየጊዜው የሚገለጽ ነው።
“የዘራሁትን ሳላነሳ በዶዘር ማሳዬን ጠረጉት፣ በዶዘር እርሻዬ ውስጥ ገብተው አረሱት፣ መሬቴን ለምን ትወስዳላችሁ? የት ልትወስዱኝ ነው? ያሸተውን በቆሎዬን መነጠሩት። ምን ላደርግ እችላለሁ። መሳሪያ የያዙ ወታደሮች ከበውኛል፣ ጠዋት ስነሳ ማሳዬ ባዶ ሆኖ አገኘሁት … ” ይህ ሁሉ የበደል ሰቆቃ ነው። በምስል ተደግፎ የቀረበ ህሊናን የሚሰብር መረጃዎች አሉ።
አንድ የአካባቢው ነዋሪ “ሰላማዊ ህዝብ፣ በቅጡ የሚለብሰው እንኳን የሌለውን ህዝብ፣ አሮጊቶችን፣ አዛውንቶችንና ህጻናትን
ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የቆዩት ለዚህ ነው? ለዚህ ኢንቨስትመንት ነው
ያ ሁሉ የተፈጥሮ ደን ወድሞ ከሰል እንዲሁን የተደረገው?

                                                                                                                      Photo: IC magazine      
 ገንዘብ ሳይሆን የከሰል ጆንያ ይዘው ክልሉን እንዲቀራመቱ የሚፈቅዱት ክፍሎች ስለጊዜና ስለዘመን ለምን አያስቡም?” ሲል ይጠይቃል። በማያያዝም “70 ከመቶ የሚሆኑት ባለሃብቶች የትግራይ ሰዎች መሆናቸውን እናውቃለን። መረጃውም አለን። እባካችሁ የተጨቆናችሁ የትግራይ ወንድምና እህቶች እባካችሁን በስማችሁ እየተፈጸመብን ያለውን በደል ተቃወሙ” ሲል ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ አስረድቷል።
አዛውንቱ ጸሐይ ለመሞቅ ታዛ ስር ቁጭ ባሉበት (በፎቶው የሚታዩት አይደሉም) ከሙሉ ቤተሰባቸው ጋር የጥይት ራት የተደረጉበት ኢንቨስትመንት አስቀድሞ የተገለጸ ቢሆንም መጨረሻው ሌብነት እንደሆነ ኢህአዴግና ራሱ ድርጅቱ ማመናቸው ተሰማ። አቶ መለስ ሲጀነኑበት የነበረው ኢንቨስትመንት አውላላ ሜዳ ላይ የተደፋ ስለመሆኑ የተጠየቁት አቶ ኦባንግ ሜቶ “እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልተሸጠው መሬት ነው” በማለት አቶ መለስ የተናገሩትን በማስታወስ “ህዝብን የማይሰማ ድርጅት ዞሮ ዞሮ ከውርደት አይድንም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሰሙት ዜና የሚጠበቅ እንደሆነ ያመለከቱት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ “ሚዲያዎች በነካ እጃቸው ስለ ሰለባዎቹም ይተንፍሱ” ሲሉ ጠይቀዋል።
ኦገስት 31/ 2013 የታተመው የጎልጉል ዜና “የኢትዮጵያን ለም መሬት ከተቀራመቱት ኢንቨስተሮች መካካል አንዱ የሆነው የህንዱ ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ለቅቆ የሚወጣበት ጊዜ መቃረቡን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታወቁ። አበዳሪዎችና ባለ አክሲዮኖች ፊታቸውን እንዳዞሩበትም ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ባዶ ዋይታ የሚያሰማው ኢህአዴግ የያዘው አዲስ አቋም ድርጅቱንና ከድርጅቱ ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው የሚባሉትን ሃሳብ ላይ ጥሏል” ሲል መዘገቡ ይታወሳል።
በዚሁ ዘገባ ላይ በቦታው ኢህአዴግና ጭፍሮቹ መካከል ሆነው የተካሄደባቸውን የመሬት ነጠቃ በመቃወምና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ጀብድ ለሰሩት “… በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችኋልና ክብር ይሁንላችሁ” ሲሉ አቶ አባንግ ያስተላለፉት መልክትም ከዜናው ጋር ተካትቶ ነበር።
“በእውቀት ላይ የተመረኮዘ፣ በእቅድ የተያዘ ትግል እያካሄድን እንደሆነ በገለጽኩበት ወቅት ካሩቱሪ በኪሳራ ከኢትዮጵያ ምድር እንደሚወጣ ተናግሬ ነበር። አሁን ጉዳዩ ያለው የኢትዮጵያን ድንግል መሬት በሳንቲም የቸበቸቡትና ያስቸበቸቡት የጥቅም ተጋሪዎችና ደላሎችን ለይቶ ለፍርድ የሚቀርቡበትን ስራ መስራቱ ላይ ነው። በህንድ ጥሪያችንን ሰምተው ትግላችንን የተቀላቀሉ ፍትህ ወዳድ እህትና ወንድሞች፣ ምስጋና ይገባቸዋል” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለ ካሩቱሪ የተሰማውን ዜና አስመልክተው ተናግረዋል።
ሰንደቅ የተሰኘው ጋዜጣ ዜና ባለስልጣኖችንና የካሩቱሪን ሃላፊ አነጋግሮ ይፋ ያደረገው ዜና ኢህአዴግን የሚያሳፍር ከመሆኑም በላይ ከዝርፊያው በስተጀርባ ያሉትን በሙሉ ያስደነገጠ ሆኗል። የጎልጉል ምንጭ እንደሚሉት የጋምቤላ ድንግል መሬት በሳንቲም ሲቸበቸብ ከጀርባ ሆነው ኮሚሽን የተቀበሉና የሚቀበሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ደላሎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የአገሪቱን ሃብት በዓይነት፣ ገንዘቧን በብድር፣ ወገኖቻቸውን በጥይት እያስደበደቡ ለባዕድ በመስጠት የፈጸሙት ወንጀል መጨረሻ በራሳቸው አንደበት ይፋ ተደርጓል።
የአክሲዮን ሽያጩና የብድር ምንጩ የደረቀበት ካሩቱሪ ንብረቱ ለሃራጅ እንዲቀርብ በዝግጅት ላይ ነው። ሰንደቅ ባይገልጸውም ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ሳዑዲ ስታር በሚባለው የግብርና ተቋማቸው ሰፊ መጠን ያለው መሬት በመውሰድ ህዝብ እንዲፈናቀል ካደረጉት ጋር እንደሚደመሩ በተለያየ ጊዜ የሚጠቆም ነው።

Saturday, October 5, 2013

ወያኔና ጽንፈኝነቱ !

ወያኔ ከጽንሰቱ ጀንሮ ፣ ውለደቱና እድግቱ የሆነው ጽንፈኝነትና ዘረኝነት ሆኖ ከሚታወቅበት ተነስተን ባሁኑ ወቅት አክራሪነትን ሲቃወም እና ሌሎችን ሲወነጅል መስማቱ <ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ> ያስብላል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔን መቃወም ብቻ ሳየሆን አለመደገፍ በራሱ ከተቃዋሚነት ጎራ ይፈርጃል ።
ነጋዴው ለሃገሪቱ የሚያስመዘግበው የንግድ ዕድገትና ለዜጎች የሚከፍተው የስራ ዕድል እና ተያያዥ አስተዋጾኦች ባሻገር ወያኔን መደገፉን በተለያየ መልኩ ካላስመሰከረና በተጨማሪም ንግድ ቤቱ ግድግዳ ላይ የማቹን ጠ/ሚ ፎቶ በመስቀል የመለስ አምልኮ ተከታየነቱን ካላረጋገጠ ያገልግሎቱ ጠቀሜታ በ ዜሮ ተባዝቶ ከንግዱ አለም ጨዋታ ውጪ ይደረጋል።
ገበሬው ማዳበሪያ ለማግኘትና ዘርቶ ለማጨድ ወያነ ባዘጋጀለት መንገድ ብቻ መግዋዝ ይኖርበታል። ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ከፍተኛ ትጽእኖ የሚደርስበት ሲሆን ከዚያም አልፎ በቀጥታ የሚያረሰው መሬት ተነጠቆ ለልመና ለስደት ሊዳረግ ይችላል።
የሀይማኖት አባቶች የመለስን አምልኮ ካለስብኩ በተቃዋሚ ፓለቲከኞች ጎራ ይምድባሉ
የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ለመቀጠር ቢጫው የወያነ የአባልነት ካርድ ከትምረት ማሰረጃና ከስራ ልምድ በላይ ዋንኛ የቅጥር መስፈረት ነው ።
ተማሪውም ከከፍተኛ የት/ም ተቐማት ተመርቆ ለመውጣት (የትምር ጠራት ችግሩ እነዳለ ሆኖ) የወያኔ አባልነት ፎርም እንዲሞላ ይገደዳል።
ፍርድ ቤቶች በህግ የበላይንት ሳይሆን ለወያኔዎች በሚመች መልኩ በንጹሀን ዜጎች ላይ በግፍ ይፈርዳሉ።
ዜጎች መኖሪአቸው ተነጥቆ ለወያኔ አባላትና ለደጋፊዎቻቸው ተሰጥቶ ለጎዳና ህይወት ይዳረጋሉ ።
ሰላማዊ ታጋዮች ፣ጋዜጠኞች ግለሰቦች የሀይማኖት መሪዎች ለወያኔ ያልተመቸ ማንኛውም ዓየነት እንቅስቃስ የሚያደርግ አካል በአሸባሪነትና በአክራሪት ተፈርዶበት እስር ቤት ይወርወራሉ።
ወያኔ አገራችንን ከተቆጣጠረበት ጀምሮ እስካሁን ድርስ ስንፈኝነትንና እና አክራሪነትን በተቀነባበረ መልኩ ሬት ሬት እያለን ሲግተን የቆየና ዘረኝነትን በየቦታው ሲሰብክና ህዝቡን ሲያወክ የኖረና በተግባር ያሳየን መሰሪ ቡድን አሁን ደሞ ባዲስ መልኩ በቲዮሪ ላስተምራችሁ ብሎ የዩነቨረሲቲ ተማሪዎችን እያስገደደ ይገኛል። ይህ ባዲስ መልኩ የሚንቀሳቀሱበት አካሄድ ጤናማ ያልሆነና ሰራአቱ የህብረተሰቡን ያመለካከት አቅጣጫ በማስቀየር የፈለጉት ኢሰባዊ የሆነወን ያገዛዝ እድሜያቸውን ለማራዘም ያቀዱት ነገር እነዳለ ያሰታውቃል።
ወያኔን የሚያሰጋው እና እንዲህ እንቀልፍ የሚነሳው የወጣቱ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እያደረገ ያለውን አምጽ እነድሆነ የታወቃል። ወጣቱ ትውልድ ዘመናዊ ባርነትን እሺ ብሎ የማይቀበል ተፈጥሮ ሰጠችውን ነጻነት በአምባገነኖች ሲነጠቅ ዝም የማይል በመሆኑ ለወያኔ አገዛዝ የማያመች ሆኖበታል ።
ሰሞኑን ሀገር ውስጥ እየታየ ያለው በተለይ ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ያጸደቀው የጸረሽብር ህግ ሳይገታው ህዝቡ ለነጻነቱ ለመታገል ዝምታን ሰብሮ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን በገለጸበት እና ባሳየው ወኔና ቁጣ ወያኔን ማሸበሩ በወቅቱ ከድሬዎችና ፈደራል ፖሊስ ካደርጉት ህገወጥ እንቅስቃሴ ማረጋገጥ ይቻላል። ወያኔን እነቅለፍ መነሳት እና እነዲ ማሸበር ልኛ የነጻነት ቀናችን መቅረቡን ከበስበስ የቆየው ለወያኔ አገዛዝ ደግሞ መውደቂያው መቅረቡ የሚያሳይ ነው ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር